Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ማክበት
ማክበት Print E-mail
Wednesday, 30 July 2008
ሼክስፒር ከጻፋቸው ቴአትሮች እንደ ዋና ሥራ ሆነው ከሚቆጠሩት አንዱ "ማክበት" የሚባለው ነው፡፡

"ማክበት" ማለት በ1040 ዓ.ም. በኤኮስ አገር ነግሦ በ1057 ዓ.ም. የሞተ ንጉሥ ነው፡፡ የነገሠውም ዘመዱ የሆነውን ዱንካን የሚባለውን ገድሎ ነው፡፡

ዱንካን መንግሥቱን ይዞ ሳለ ማክበት (ታን) የሚባል ከፍ ያለ የማዕረግ ሥም ተቀብሎ ያገለግለው ነበር፡፡ በዱንካን መንግሥት ከግዛቶቹ ባንድ አገር ያሉ ሕዝቦች አምፀው ሁከት ስላነሱ በዚሁ ምክንያት በሆነው ውጊያ ማክበት በፈፀመው የጀግንነት ሥራ ተመሰገነ፡፡

 (ከበደ ሚካኤል፣ ታላላቅ ሰዎች፣ 1964)

ንገረኝ

እኔነቴን ቃኘኝ በረቀቀ እይታ፣
ውስጣዊ እኔነቴን ዳስሶ በሚፈታ፡፡
የአርቆ ማስተዋል ብልሀት ብርታቴ
. . . አለዚያም ድክመቴ፣
መሰረት ነውና ለነገ እኔነቴ፣
እንከኔን ንገረኝ ባክህ መስታወቴ፡፡
እውነት ተናጋሪ ስላጣሁ ፈልጌ፣
እባክህ መስታወት አንተ ሁነኝ ጓዴ፡፡
 
(ትዕግሥት ምትኩ፣ የጠፈር አበባ፣ 1999)

ወንጀልና ፍትሐ ብሔር


አንድ ድርጊት የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ሐላፊነትን በአንዴ ሊያስከትል ይችላል፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ አንድ ድርጊት ከሁለት አንዱን ሐላፊነት ብቻ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለምሳሌ የመግደል ሙከራ ጉዳት ሳይደርስ ሊፈፀም ይችላል፡፡ አንዱ ሌላውን ሰው በበዛበት ሥፍራ ተኩሶ ቢስተው የተተኮሰበት ሰው እንኳን ጉዳት ሊደርስበት ወደ እሱ እንደ ተተኮሰበት እንኳን ላያውቅ ይችላል፡፡ ይህ ድርጊት ከውል ውጭ ያለ ሐላፊነትን ባያስከትልም በወንጀል ሕግ ግን የመግደል ሙከራ በመሆኑ ያስቀጣል፡፡ አንድ ድርጊት ሁለቱንም ሐላፊነቶች ወይም ከሁለት አንዱን ብቻ ማስከተል አለበት ብሎ ለመደንገግ ቀላል የሆነ ቀመር መጠቀም ባይቻልም ድርጊቱ የጎዳው የግለሰብን መብት ብቻ ከሆነና ጉዳቱም አነስተኛና ሕብረተሰቡም ብዙም የማያወግዘው ከሆነ ለዚህ ድርጊት የፍትሐ ብሔር ሐላፊነት ብቻ በቂው ይሆናል፡፡ በተጨማሪም የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር መንግሥትንም ሆነ ሕብረተሰቡን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ በመሆኑ ማለትም ፖሊስ፣ ዐቃቤ ሕግ፣ ፍርድ ቤቶች ወዘተ. የሚሳተፉበት በመሆኑ ለድርጊቱ የፍትሐ ብሔር ኃላፊነት ለምሳሌ ካሣ መክፈል በቂ ሆኖ ሲገኝ የወንጀል ኃላፊነት አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ሕብረተሰቡንም ከወጪ ያድናል፡፡

 (ፀሐይ ወዳ፣ የወንጀል ሕግ መሠረታዊ መርሆች፣ 1994)

የመከራከር ድርሰት


የመከራከር ድርሰት የተባለው ባለጋራውን ለመርታት ወይም ለማሸነፍ የሚዘጋጀው የንግግር ጦርነት መከላከያ ነው፡፡ ስዚህ እያንዳንዱ ተከራካሪ ተማሪ ንቃትና ቀጥተኛነት ባለው አቋቁሙ ተመልካቾችን ለማስደሰት በተመረጠው ንግግሩ አዳማጭዎቹን ለማፍዘዝ በተለይም ዳኛዎቹን ለመማረክ፣ ከተሰጠው ርእስ ውጭ በምንም ነገር ሳይወጣ ከስድብና ከብልግና ቃል በመራቅ ሥነ ሥርዓትን ጠብቆ በመከራከር ብልጫ ያገኝ ዘንድ በተቻለው መጠን መጣርና መትጋት አለበት፡፡

 (ጽጌ ገብረ ኪዳን፣ የአደራረስ መምሪያ፣ 1958)

የዘመናዊነት ኢትዮጵያ መመሥረት

ከ19ኛው መቶ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ተበታትነው የነበሩትን የኢትዮጵያ ግዛቶች ከማዋሐዱ ተግባር ተቀዳሚ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይሁን እንጂ የተለያዩ ነገሥታት ተግባሩን በተለያየ መንገድ ነበር የሚተረጉሙት፡፡ ለቴዎድሮስ አንድነት ማለት ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት መመሥረት ማለት ነበር፡፡ ለዮሐንስ ደግሞ የውስጥ ነፃነት ያላቸው የክልል ገዢዎችና የበላይነቱ የታወቀለት ንጉሠ ነገሥት ተከባብረው የሚኖሩበት ሥርዓት ማለት ሆነ፡፡ ቴዎድሮስ መቅደላ፣ ዮሐንስ መተማ ላይ ሲሞቱ ሁለቱም ስልቶች የተጠበቀውን ውጤት እንዳላመጡ ግልጽ ነበር፡፡ ቴዎድሮስም ማዕከላዊ መንግሥት መመሥረት አልቻለም፡፡ ዮሐንስም የበላይነቱ አልከበር ማለት እንዳሳበደው የማህዲስት ጥይት እራት ለመሆን በቃ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሥታት ዓላማቸው ቢከሽፍም የነደፉት ሐሳብና የተለሙት መንገድ በተከታዩ ትውልድ ላይ አሻራቸውን ሳይተዉ አላለፉም፡፡

 (ባሕሩ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1947 እስከ 1983፣ 1999)

የፍቅር ዜማ

አንድ ገጣሚ የፃፈው የፍቅር ዜማ በጣም ማራኪ ነበር፡፡ ይህንኑ ዜማ ያባዛና ለሴትና ወንድ ጓደኞቹ እና ወዳጆቹ ይልክላቸዋል፡፡ አንዲት ከአድማስ ባሻገር የምትገኝ ወጣትም አንዱ ቅጂ ይደርሳታል፡፡

በአንድ ወይም በሁለት ቀናት ውስጥ አንድ መልዕክተኛ የወጣቷን ደብዳቤ ይዞ ይመጣል፡፡ "በፃፍክልኝ የፍቅር ዜማ ውስጤ በጥልቅ እንደተነካ ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡ አሁን ና እና አባቴንና እናቴን ተዋወቃቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ ትጭጭታችን እንወያለን" የሚል መልዕክት ነበር የላከችው፡፡

ባለቅኔው ለደብዳቤዋ እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ "ወዳጄ፣ ማንኛውም ወንድ ለማንኛዋም ሴት የሚያንጐራጉርላትን ከአንድ ገጣሚ ልብ የፈለቀ የፍቅረ ዜማ ነው የላኩልሽ"

እሷም ዳግመኛ መልሳ ፃፈችለት፡፡ "ግብዝ እና ውሸታም ነህ" ከዛሬ ጀምሮ እስክሞት ድረስ በአንተ ምክንያት ሁሉንም ገጣሚያን ጠላሁዋቸው"

(ተስፋሁን ምትኩ እና ሀብታሙ ተስፋዬ (ትርጉም"፣ የጥበብ መንገድ፣ 1998)

ከንግግር በፊት

ንግግሩ ከመጀመሩ ቀደም ብሎ ያሉት ጥቂት ሰኮንዶች በንግግሩ ዓላማ ላይ ጉልህ ሚና አላቸው፡፡ ምክንያቱም በተናጋሪውና በአድማጩ መካከል ግንኙነት የሚመሰረትበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡

ተናጋሪው ከአድማጮቹ ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠሩ ንግግሩን ስኬታማ ያደርግለታል፡፡ ይህም ተቀባይነት ለማግኘትና ውጤታማ በሆነ መንገድ ንግግሩን ማስተላለፍ እንዲችል ይረዳዋል፡፡ ተናጋሪው ከአድማጮቹ ጋር ያለው ግንኙነት እንደ አንድ ተናጋሪ ሆኖ ሲመለከተው እነርሱ የሚያሳዩትን እያንዳንዱን የስሜት ለውጥ እስከሚሰማው ድረስ በጣም ሊቀርባቸው ይገባል፡፡ ወዳጅነት ያለው አቀራረብና ሞቅ ያለ ፈገግታ ከአድማጮች ጋር የሰመረ ግንኙነት እንዲኖር በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያበረክታል፡፡

ተናጋሪው ንግግሩን ማስተላለፉ ከጀመሩ በፊት የሚወስደው እርምጃ "ጥርጣሬን መግፈፍ" ይሆናል፡፡ "ከፍትፍቱ ፊቱ" እንዲሉ ተናጋሪው ከንግግሩ አስቀድሞ አድማጩ እርሱን እንዲቀበለው የሚያስችለውን ግንኙነት በመልካም ገጽታ መመሥረቱ የግድ ነው፡፡ "ፈገግ ማለት የማይችል መደብር መቆም የለበትም" የሚለው የቻይናዎች ምሳሌም ይህንን ሃሳብ የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡

(ቃልኪዳን አምባቸው (ትርጉም"፣ የንግግር ጥበብ፣ 1996)

ነገደ ኩሽ

በጥንታዊ የአፍሪካ ሥልጣኔ ከታወቁት፣ ከአፍሪካ ሕዝቦች መሃል አንዱ በቀይ ባህር በስተደቡብ የሚኖሩ በንግድ የሚተዳደሩ ነገደ ኩሽ በመባል የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ500 ዓመት ጀምሮ እነዚህ በኢትዮጵያውያኖች ከቀይ ባህር ባሻገር ከሚገኙ ጎረቤቶቻቸው ሳባውያን በመባል ከሚታወቁት ከአረቦች ብዙ ተምረዋል፡፡ በኋላም ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በንግድ ሥራ ከገቡት ሳባውያን መካከል ከፊሎቹ እዚሁ ስለቀሩ የአገሬው ተወላጅ ከሆኑት ከነገደ ኩሽ ጋር ተቀላቅለው (ተደቅለው) በመኖራቸው የነበራቸውን ዕውቀት በማካፈል የአካባቢው ሥልጣኔ ከበፊቱ የበለጠ ዳበረ፡፡ ሁሉም በኢትዮጵያዊነታቸው ቢታወቁም ሥነ ጽሑፋቸው እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በሳባውያን ቋንቋ ነበር፡፡

(አለምሰገድ ቦጋለ፣ የኤርትራው እንቆቅልሽ፣ "

ገ    ራ    ገ     ር
ህገ ወጥ አስተላላፊዎች የመሬት ውስጥ ቱቦን ተጠቀሙ


ከአንድ ግዛት ወደ ሌላ ግዛት በህገ ወጥ ሁኔታ ዕቃዎችን ለማዘዋወር ሲሉ ሁለት ቤቶችን በ600 ሜትር የመሬት ውስጥ ቱቦ እንዳገናኙ የቻይና ፖሊስ ይፋ አደረገ፡፡

በእለታዊው ጉዋንዙ ዘገባ መሠረት ከሆነ በሆንግ ኮንግ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ከዋናው የቻይና መሬት በረከሱ ዋጋዎች ይገኛሉ፡፡ ይህ የህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች 1.8 ሜትር ጥልቀት ያለው ቱቦ እቃዎችን ለማዘዋወር የሚውል መሆኑንም ፖሊስ ደርሶበታል፡፡

በቻይና ሽንዝሄንግ ከተማ የነበረውን ገበያ ህገ ወጥ ዝውውር እንደተከናወነበት ለፖሊስ የተጠቆመው ከአካባቢው ነዋሪዎች ነበር፡፡ በተለይም የሞባይል ቀፎዎችና የኮምፒውተር መገጣጠሚያዎች በብዛት ተላልፈውበታል፡፡

በቱቦው ከሆንግ ኮንግ የተላለፉት ቁሳቁሶች ዋጋ ወደ 450"000 ፓውንድ የተገመተ ሲሆን 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ጉዳዩ የፍርድ ቤት ውሳኔን እየጠበቀ ነው፡፡

የ44 ዓመቷ ወይዘሮ 18ኛ ልጇን ተገላገለች

ኑሮዋን በካናዳ ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ያደረገችው የሮማኒያ ስደተኛ ሊቪያ በ44 ዓመቷ 18ኛውን ልጇን በመገላገሏ የግዛቷ የ2ዐ ዓመቱ ምርጥ ወላድ እናት ተሰኘች፡፡

የወይዘሮዋ ባለቤት አሌክሳንድሩ አይኦንስ የልጆቻቸውን ቁጥር ያልወሰኑት በእግዚአብሔር ባላቸው እምነት የተነሳና ሁሉንም የመምራትና የመወሰን ስልጣን የፈጣሪ መሆኑን ጠንካራ እምነት ስላላቸው መሆኑን ለአናኖቫ ገልጿል፡፡

ጥንዶቹ 10 ሴቶችና 8 ወንዶች ያላቸው ሲሆን አይኦንስ የወንዶቹ ቁጥር ከሴቶቹ ጋር እንዲመጣጠን ፍላጎት እንዳለው ገልፆ ሁሉም ልጆች ጤነኛና ደስተኞች እንዲሆኑ ላደረገው እግዚአብሔር ምስጋና አቅርቧል፡፡

ቡድኖች በነዳጅ ማደያዎች ለአነስተኛ ዋጋ ሊፀልዩ ነው

ሁለት ቡድኖች በአሜሪካ ሴንት ልዊስ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ውስጥ ፀሎት ሊያካሂዱ የታቀደላቸው ሲሆን በስርዓቱ ላይ የነዳጅ ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ ላደረገው ፈጣሪ ምስጋና ለማቅረብና ይበልጥ ዋጋ እንዲቀንሱ በፀሎት ለመጠየቅ የታለመ ነው፡፡  ከሁለቱ የፀሎት ቡድኖች የአንዱ ምክትል ኃላፊ ዳረል አሌክሳንደር የፀሎት ሥነ ሥርዓቱ በመጪው ሰኞ በሞቢል የነዳጅ ማደያ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡

ከፀሎት ቡድኖቹ አባላት መካከል አንዳንዶቹ "ነዳጅ መግዛታችንን በመቀጠል በፀሎትና በመዝሙራችን ነዳጅን በርካሽ ለማግኘት ጌታችንን እንጠይቃለን" ብለዋል፡፡

ከጉዳዩ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነውና ከዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የመጣው ሮኪ ትዋይማን ጥረቱን ያስጀመረው እሱ ሲሆን "ፖለቲከኞች የነዳጅ ዋጋን ለመቀነስ ካልቻሉ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው" ብሏል፡፡

የፀሎት ቡድኖቹ ፀሎታቸው እየረዳቸው እንደሆነና ለዚህም የአንድ ጋሎን ነዳጅ ዋጋ ከ4 ዶላር በታች እየወረደ መሆኑን እንደጠቀሱ ያሁ ዘግቧል፡፡

ጠበቃው ወሲብ ነክ ፊልም ለመሥራት አቀደ


በአእምሮ ውጥረት ረጅም የህመም እረፍት የወሰደው ጠበቃ የወሲብ ነክ ፊልም ተዋናይ መሆን እንደሚፈልግ በኢንተርኔት አገልግሎቱን እያስተዋወቀ ነው፡፡

በክራውን የልዩ ወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የነበረው የ56 ዓመቱ ክሊፎርድ አሊሰን ወደ አዲስ የሙያ ምርጫ መግባቱን የሥራ ባልደረቦቹ እንዳስገረመ ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡

አሊሰን ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት ሲሆን ለቤተሰቡ እንደነገረ ያስታወቁት ዶክተሩ የአሊሰንን ውሳኔ "ከጤና አንፃር አስፈላጊ ነው" ብለውታል፡፡

አሊሰን መደበኛ የትወና ሥልጠና ያልወሰደ ሲሆን በተለያዩ ፊልሞች ላይ ግን የተሳትፎ ልምድ አለው፡፡ የአሰሪ ድርጅቱ ቃል አቀባይ "ሰራተኞቻችን ተጨማሪ ሥራ ለመስራት የፅሁፍ ፈቃድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ አሊሰንን በሰራው ሥራ አግኝተነው እንዲያጣራልን እናደርጋለን" ብለዋል፡፡
 
< Prev   Next >