| የቲ.ቪ.ቲ ኮሌጆችን የሚገነቡ... |
|
|
| Sunday, 03 August 2008 | |
|
የቲ.ቪ.ቲ ኮሌጆችን የሚገነቡ ኮንትራክተሮች እየጠፉ ነው
በኃይሌ ሙሉ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችን ለመገንባት ስምምነት የተፈራረሙ ኮንትራክቶች የቅድመ ክፍያ ወስደው ስራቸውን ከጀመሩ በኋላ ግንባታውን አቋርጠው እንደሚጠፉ ተገለፀ፡፡ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ አቶ ጋሻው ገዳ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት በአላጌ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ ኮሌጆችን ለመገንባት ስምምነት የተፈራረሙ ኮንትራክተሮች የዋጋ ንረቱን እንደምክንያት በመጥቀስ ግንባታቸውን አቋርጠዋል፡፡ አንዳንዶችም ቅድሚያ ክፍያ ከተቀበሉ በኋላ ሥራውን ጥለው ጠፍተዋል፡፡ ከስድስት አመት በፊት ተጀምሮ የነበረው የአላጌ ኮሌጅ የቤተ መጻህፍትና የመንገድ ግንባታም እስካሁን ድረስ ቆሟል፡፡ መንግሥት ለቲቪቲ ፕሮጄክት ከፍተኛ በጀት ቢመድብም የተመደበው በጀት በአግባቡ ጥቅም ላይ ባለመዋሉ ተመላሽ እንደሚሆን የገለጹት አቶ ጋሻው በጀቱ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዳይውል ችግር የፈጠሩት በግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆቹ የተለያዩ ግንባታዎች ለማከናወን የተስማሙ ኮንትራክተሮች በፈጠሩት ችግር ነው፡፡ አቶ ጋሻው እንደ ምሳሌ ሲጠቅሱም ፕሮጀክቱ በ1995 ዓ.ም ከተመደበለት 424 ሚሊዮን 402 ሺ 296 ሚሊዮን 402 ሺ 296 ብር ውስጥ በጥቅም ላይ የዋለው 257 ሚሊዮን 8ሺ 675 ብር ብቻ ነው፡፡ አስተባባሪው እንዳሉት የአላጌ ኮሌጅን ቤተ መፃህፍት ለመገንባት ስምምነት ፈርሞና የቅድሚ ክፍያ ተቀብሎ የነበረው አዋሽ የተባለ የመንግሥት ኮንስትራክሽን ድርጅጽ ግንባታውን አቋርጧል፡፡ አዋሽ ከለቀቀ በኋላ ግንባታውን ለማከናወን ተዋውሎ የነበረው ሊበን የተባለ ሌላ የግል የግንባታ ድርጅትም ትንሽ ስራ ከሰራ በኋላ ቅድሚያ ክፍያ ተቀብሎ ቦታውን ጥሎ ጠፍቷል፡፡ በትግራይና በአፋር ክልሎችም ከዋጋ ንረት ጋር በማያያዝ ስራ የማቋረጥ ሁኔታ ከተስቷል፡፡ “ኮንትራክተሮቹ ስራቸውን በአግባቡ ቢያከናውኑ ኑሮ በዋጋ ንረቱ ምክንያት ራሳቸውን ለኪሳራ ሊያጋልጡ አይችሉም ነበር” ያሉት አቶ ጋሻው የግንባታ ስራቸውን በማቋረጥ ጥለው የጠፉት ድርጅቶች ጉዳይ ለሕግ እንደተላለፈ ተናግረዋል፡፡ የዋጋ ንረቱን ምክንያት በማድረግ ከአንዳንድ ድርጅቶች ጋር ድርድር እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ዋና አስተባባሪው በትግራይ ክልል ግንባታ ከሚያከናውኑ አንድ የግንባታ ድርጅት ጋር በተደረገ ድርድር ኮንትራክተሩ እና የእርሳቸው ቢሮ የሚቆጣጠረው ተጨማሪ ገንዘብ ተመድቦ የተጀመረው ስራ የሚያጠናቅቅበት ሁኔታ መመቻቸቱን አስረድተዋል፡፡ የአላጌ ኮሌጅን መንገድና ቤተመፃህፍትን ለማሰራት ግን ሶስተኛ ጨረታ ከማውጣት ውጭ ሌላ አማራጭ አለመኖሩን አስታውቀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |