Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Wednesday
Aug 20th
Home arrow Sections arrow በሞባይል የድምፅ እና የቪዲዮ...
በሞባይል የድምፅ እና የቪዲዮ... Print E-mail
Sunday, 03 August 2008
በሞባይል የድምፅ እና የቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት የሙከራ ሽያጭ ሊጀምር ነው

በጋዜጣው ሪፖርተር

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዜድ.ቲ.ኢ ከተባለ የቻይና ኩባንያ ጋር ባደረገው የቪንደር ፋይናንሲንግ ስምምነት መሰረት ሲያከናውን የነበረው የመጀመሪያ ዙር በሞባይል የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪ (WODMA) ሞባይል ኔትዎርክ ፕሮጀክት ዝርጋታ በማጠናቀቅ በአዲስ አበባ የሙከራ የሽያጭ አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው፡
በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ምዕራፍ ከሚዘረጋው በሞባይል የድምጽና የቪዲዮ ጥሪ ኔትወርክ ውስጥ በቅድሚያ ውሱን አቅም በሙከራ ደረጃ ለሽያጭ እንዲውል ይደረጋል፡፡

አገልግሎቱ በመጀመሪያ በቅድመ ክፍያ ሥርዓት የሚሰጥ እና የኔትወርክ ሽፋኑ በአዲስ አበባ ከተማ በተመረጡ አርባ ዘጠኝ አካባቢዎች ሲሆን ከእነዚህ 45 ቦታዎች ውጪ የቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት የማይኖርና የድምፅ አገልግሎት ግን የሚያገኙ መሆኑን ለተጠቃሚው ህብረተሰብ አስታውቋል፡፡ በቀጣይም የአከፋፈል ሥርዓቱ የድህረ ክፍያን ሥርዓት የሚጨምር እንደሚሆን እና የኔትወርክ ሽፋኑም ወደፊት በሙሉ አዲስ አበባ አካባቢዎች የሚስፋፋ ይሆናል፡፡

ለደንበኞች የሲም ካርድ አቅርቦት የሚደረገው በቴሌኮሙኒኬሽን የአገልግሎት ሽያጭ ማዕከላት ሲሆን፣ የ”“ የምትክ ሲም ካርድ፣ የቅድመ ክፍያ ቫውቸር ካርዶችን እና ሲም ካርዶች አቅርቦት በአዲስ አበባ በሚገኙ የቴሌኮሙኒኬሽን የሽያጭ ማዕከል ይከናወናል፡፡

ደንበኞች የሞባይል አገልግሎት ክፍያ ሂሳባቸውን ለመሙላት 909 ላይ መደወል የሚጠበቅባቸው ሲሆን፣ የሚጠቀሙት ቀፎ የሚከተለውን መስፈርቶች ያሟላ መሆን አለበት፡፡

Frequency bands and channel spacing
* Mobile Transmit = 1920 - 1980 MHZ
* Mobile Receive = 2110 - 2170 MHZ
* Channel Spacing - 5 MHZ

በቀጣይነት የቪዲዮ፣ የዳታ እና የድምጽ መልዕክቶችን ማስተላለፍ እና መቀበል (Multimedia Message service MMS) / እና የድምጽ መልዕክት (Voice mail) አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችለውን ኔትወርክ የማብቃት /upgrading/ ሥራ እየተሠራ በመሆኑ ወደፊት ባለው ቀጣይ ጊዜ የተጠቀሰውን አገልግሎት በአዲስ አበባ ለመጀመር ይቻላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኮርፖሬሽኑ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በሞባይል የድምጽ እና የቪዲዮ ጥሪ አገልግሎት የተቀመጠ ታሪፍን በተመለከተ አገልግሎት ፈላጊዎች ብር 600.00 የደንበኝነት አገልግሎት ክፍያ በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የፍጆታ ታሪፍ በተመለከተ ለድምጽ ጥሪ በደቂቃ 0.72 ሣንቲም፣ በቅናሽ ሰዓት ከሰኞ እስከ እሁድ ከምሽቱ 2 - ጧት 2 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ፣ እሁድ፣ የበዓል ቀናት) 0.30 ሣንቲም ሲሆን የቪዲዮ ጥሪ በደቂቃ 2 ብር ከ70 ሳንቲም መሆኑን ገል”ል፡፡ ይኸው የድምፅ ጥሪ አገልግሎት ለጅቡቲ በደቂቃ 7 ብር ከ72 ሣንቲም፣ ለሌሎች የዓለም አገራት 10 ብር ከ72 ሣንቲም ሲሆን የቪዲዮ ጥሪ ለጅቡቲ በደቂቃ 28 ብር ከ95 ሣንቲም፣ ሌሎች ዓለማት 32 ብር ከ16 ሣንቲም መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህ አገልግሎት ዙሪያ የተሰጠን መግለጫ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ውስጥ አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው አካባቢዎች 49 ናቸው፡፡

እነዚህም ናይል ኢንሹራንስ ቃሊቲ አካባቢ፣ ሀና ማርያም ላፍቶ አካባቢ፣ ጎተራ፣ ጎፋ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ቴሌ ማሰልጠኛ፣ ተሻለ ጋራዥ አካባቢ፣ ሳርቤት፣ ዳቢ ህንጻ ሳይ ኬክ ቤት አካባቢ፣ ራስ ብሩ አካባቢ፣ ኦሎምፒያ፣ ዓለም ባንክ፣ ቦሌ፣ አፍሪካ ህብረት አካባቢ፣ ፍላሚንጎ፣ ኒያላ ሞተር፣ አልታ ህንጻ ሜክሲኮ አካባቢ፣ አውራሪስ ሆቴል፣ መስቀል አደባባይ፣ ባቡር ጣቢያ አካባቢ፣ ውሃ ልማት ሚኒስቴር አካባቢ፣ ፍልውሃ፣ ጨፌ ሜዳ፣ ማይክሮዌቭ አካባቢ፣ ኮካ ማዞሪያ እና አብነት አካባቢ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አካባቢ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት አካባቢ፣ የካ፣ ጭድ ተራ፣ ራስ አምባ ሆቴል፣ ጋራድ ህንጻ፣ ለይላ ህንጻ፣ እሪ በከንቱ፣ መርካቶ፣ ቤልኤር ሆቴል አካባቢ፣ አማኑኤል ቤ/ክርስቲያን አካባቢ፣ አራዳ፣ ከሊፋ ህንፃ፣ ጎጃም በረንዳ፣ አዲስ ከተማ፣ ቀበና፣ አራት ኪሎ፣ አራዳ ጊዮርጊስ አካባቢ፣ ሞተራ ሆቴል፣ ጃማይካ፣ መድሃኒዓለም ት/ቤት፣ እንጦጦ ት/ቤት ናቸው፡፡
 
< Prev   Next >