| ኮርፖሬሽኑ ለንግዱ ህብረተሰብ... |
|
|
| Sunday, 03 August 2008 | |
|
ኮርፖሬሽኑ ለንግዱ ህብረተሰብ የሚሆን ሰፊ የሥራ እድል እንዳለ አስታወቀ
ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ምህረት ደበበ ይህንን የገለፁት ከትናንት በስቲያ የገጠር ኤሌክትሪክ መስፋፋትና ለኢንቨስትመንት የሚፈጥረው እድል በሚል ርእስ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ባዘጋጀውና የንግዱ ህብረተሰብ ተሳታፊ በሆነበት የምሣ ላይ የውይይት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡ እንደ አቶ ምህረት ገለፃ በዩኒቨርሳል አክሰስ ፕሮግራም በዓመት የ2.5 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት የሚጠይቅና በመጪዎቹ አስር ዓመትም ይህ የኢንቨስትመንት መጠን ወደ 120 ቢሊዮን ብር ይደርሳል ተብሎ የሚገመት በመሆኑ በዚህ ሰፊ የኢንቨስትመንት ውስጥ የንግዱ ህብረተሰብ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የሥራ እድሎች እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡ ፕሮግራሙ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ለንግዱ ህብረተሰብ የማሳየት የሚችል አሀዛዊ መረጃ ባያስቀምጡም በኮንስትራክሽን ሥራዎች፣ የስርጭት መስመሮችን የማምረትና ማዳረስ ሥራዎች፣ ትራንስ ፎርመሮች፣ ኬብሎች፣ ብረታ ብረቶች የማምረት ሥራዎች፣ የኮንክሪትና የእንጨት ፖሎች ምርት፣ ለአገር ውስጥ ግልጋሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ ውጤቶች ምርት፣ የክፍያ መሰብሰብ አገልግሎቶች የጥገናና የመሳሰሉት ሥራዎች ሁሉ ለንግዱ ህብረተሰብ የሥራ እድል እንዲፈጠረላቸው እንደሚያደርግ አቶ ምህረት ገልፀው በተለይ እነዚህ የተጠቀሱት ሥራዎች በአሁኑ ወቅት ከ1800 በላይ የሚሆኑ ከተሞች የኤሌክትሪክ ሽፋን በማግኘታቸው አገልግሎቱ በቂ አለመሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን እስካሁን ድረስም የአገልግሎት አድማሱን ለማስፋትና 800 በላይ የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ለማስፈፀም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሃያ አምስት ከማዳረሱ ውል መፈራረማቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ ያለው ከፍተኛ ፍላጐት በመንደሮችና መሰል አቅጣጫዎች የጥገናና እንጨት ሥራ የሚጠይቁ በመሆኑ በኢንጂነሪንግ በህግ በኢኮኖሚክስ በማህበራዊ ዘርፍ ያሉና የማማከር አገልግሎት የሚሰጡ መስኰች በዚህ ፕሮግራም መሠረት ሰፊ የሥራ እድል መኖሩን አስረድተዋል፡፡ "የትራንስፖርት የባንክ ኢንሹራንስና የጤና አገልግሎት መስኰችም የንግዱ ማህበረሰብ የማያተኩርባቸውና ሰፊ የገበያ ዕድል ያላቸው ናቸው፡፡ ያሉት አቶ ምህረት እነዚህ ዘርፎች በተያዘው ሁሉ አቀፍ የኤሌክትሪክ ስርጭት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ኰንትራት በመያዝ ተጠቃሚ መሆን በመቻላቸው በአገራችን ያሉ የንግድ ኩባንያዎች በኤሌክትሪክ ዘርፍ ለመሰማራት ገበያውን መጋራት ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ በመጪዎቹ ጊዜያት የገጠሩ ክፍል ዋና የቢዝነስ ማዕከል ይሆናል ተብሎ የሚገመት በመሆኑም ለንግዱ ህብረተሰብ አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ሊሆን እንደሚችል አስረድተው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ከ300"000 በላይ ደንበኞችን በዓመት በኤሌክትሪክ መስመር ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ በመሆኑ ነው፡፡ የፋብሪካው ዘርፍ ለምንፈልገው የሃይል ስርጭት የገበያ ሽፋን እየሰጠ ይገኛል፡፡ ያሉት አቶ ምህረት በተለይ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የራሱ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ነው፡፡ የሃይል አቅርቦት ሴክተር በተፈጥሮው ፈርጀ ብዙ እንደመሆኑ መጠን የመሃንዲሶች የኢኮኖሚና ፋይናንስ አካባቢዎችን የማማከር አገልግሎት እያገኘን እየሰጡ መሆኑ በተለያየ አቅጣጫ፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ የትኞቹ ኢንዱስትሪዎች የጥራት ደረጃ ያሟላሉ የሚል ጥናት እያደረግን ሲሆን በተለይ ከሃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጡ ይችላሉ የተባሉ ቆጣሪዎችን በአዲስ መልክ ለመተካትም ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በድሬዳዋ፣ መቀሌና ባህርዳር ከተሞች ትልቅ ፕሮጀክት በዚሁ ዙሪያ እየካሄደ መሆኑንና ዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግበት ይህ ፕሮጀክት አገሮቹን ቆጣሪዎች በተሻሻሉት ለመተካት የሚደረግ እንቅስቃሴ ነው፡፡ "በአሁኑ ወቅት የደንበኞችን አገልግሎት ለማስፋፋት ከ20"500 በላይ ሠራተኞችን እያንቀሳቀስን እንገኛለን" ያሉት አቶ ምህረት "ደንበኛ ንጉሥ ነው" የሚለውን አባባል በተጨባጭ ለመተግበር ጥረት እየተደረገ እንደሆነም ተወስቷል፡፡ የነዳጅ ኃይል ፍጆታ ኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረውን ጫና በተመለከተ በቅርቡ ይፋ የተደረጉ ኢኮኖሚ መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት በአፍሪካ ሁለት በመቶ የሚሆነው ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት በነዳጅ ሳቢያ የሚባክን ሲሆን በኢትዮጵያ አንድ በመቶ ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ለክስረት እንደሚደረግም ተጠቁሟል፡፡ እንደ አቶ ምህረት ገለፃ በአሁኑ ወቅት ኮርፖሬሽኑ ለኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚያስከፍለው ክፍያ ከሌሎች አገራት ክፍያ ጋር ሲወዳደር ዝቅተኛ መሆኑንና በዚህ የሃይል ማመንጨት ሥራ ላይ የግሉ ዘርፍ ለመግባት ያልደፈረውም አዋጭ አይሆንም ከሚል እምነት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በዚህ ዘርፍ ያለውንም ግንባታ በማካሄድ ላይ ያለው መንግሥት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ ለኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚከፈለው ክፍያ ዝቅተኛና በመንግሥት የሚደጐም መሆኑን ያስታወሱት አቶ ምህረት ሃይል ለማመንጨት ኢንቨስት የሚደረገውና ከአገር ውስጥ ለኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚከፈለው ክፍያ መካከል ሰፊ ልዩነት አለው፡፡ በሌላም በኩል የሃይል ብክነትና ተጠቃሚዎች ሃይልን ቆጥቦ የመጠቀም ባህል አነስተኛ መሆኑንም ተችተዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |