Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ፋልኮን የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ...
ፋልኮን የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ... Print E-mail
Wednesday, 06 August 2008
ፋልኮን የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ የነዳጅ ፍለጋ ስምምነት ነገ ይፈራረማል

በቃለየሱስ በቀለ

የፌዴራል ማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ፋልኮን የተባለ የእንግሊዝ ኩባንያ በነዳጅ ፍለጋና ልማት ስምምነት ላይ ነገ ይፈራረማሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጣና ዙሪያ የነዳጅ ፍለጋ ለማካሄድ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ድርድር ሲያደርግ መቆየቱን፣ የነዳጅ ፍለጋና ልማት ፈቃድ ለማግኘት ለሚኒስተሮች ምክር ቤት ቀርቦ በቅርቡ መጽደቁን ምንጮች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡

ስምምነቱን የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑና የኩባንያው ኃላፊ (ተወካይ) በነገው ዕለት ይፈራረማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ነዳጅ ይገኝባቸዋል ከሚባሉት አምስቱ ቦታዎች (ሴዲመንተሪ ቤዚን"፣ ጋምቤላ፣ ኡጋዴን፣ ኦሞ፣ አባይሸለቆ፣ ትግራይና አፋር አካባቢዎች መካከል ጣና ዙሪያ አንዱ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡
 
< Prev   Next >