| የጃኮብ ዙማ ጉዳይ በመጪው... |
|
|
| Wednesday, 06 August 2008 | |
|
የጃኮብ ዙማ ጉዳይ በመጪው ጥቅምት ይወሰናል
ዙማ የፖለቲካ ሸፍጥ ሰለባ እንደሆኑና በቀጣዩ ዓመት ሐምሌ ወር በሚደረገው ኘሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዳያሸንፉ የተቀነባበረ ሴራ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ "በህይወቴ ምንም ነገር ፈርቼ አላውቅም" ሲሉ ባለፈው ሰኞ ፒተርማሪትዝበርግ በሚገኘው ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የተደመጡት ዙማ የፀረ-አፓርታይድ ትግል መለያ የሆነውን ዘፈን አቀንቅነዋል፡፡ ትላንት ጉዳዩን ለማየት የተቀመጡት ዳኛው ኒኮልሰን ለህዳር 8 የወንጀል ክሱን ለመስማት በጊዜያዊነት የቀጠሩ ሲሆን ጉዳዩን በመቀጠልና ባለመቀጠል ጉዳይ ላይ ለመወሰን ግን መስከረም 12 ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡ የዙማ ጠበቆች በክስ ሂደቱ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ሲገልፁ ተቃዋሚዎቻቸው ደግሞ ጉዳዩን ዙማ ኘሬዚዳንት እስኪሆኑ ድረስ እያሸጋገሩት ነው ብለው ይከሳሉ፡፡ ዙማ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ተከሰው ነፃ የወጡባቸው ጉዳዮች ሲኖሩ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡ የኤምዲሲ መሪዎች ለሰላም ድርድሩ የመደራደሪያ ነጥቦች አቀረቡ የዚምባቡዌ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ኤምዲሲ ከሃገሪቱ ገዢ ፓርቲ ዛኑፒኤፍ ጋር እያደረጉ ባሉት የስልጣን መጋራት ድርድር የፓርቲው መሪ በመንግሥት የስራ አስፈፃሚ ውስጥ ቦታ ካልተሰጠው እንደማይቀበል ግልፅ አድርጓል፡፡ የአምዲሲ ፓርቲ መሪ ሞርጋን ቻንጋራይ የዚምባቡዌ ጠቅላይ ሚኒስትር ካልሆኑ ድርድሩ እንደማይቀጥል ከፍተኛ የኤምዲሲ ባለሥልጣናት ለኬንያው ፣ዘ ኔሽን፣ ጋዜጣ ገልፀዋል፡፡ የመንግሥት ባለስልጣናት በድርድሩ ጉዳይ መግለጫ መሰጠትን ሁለቱም ተደራዳሪ ወገኖች ለመተው መስማማታቸው ይገልፃሉ፡፡ ድርድሩ ባለፈው ሰኞ መፈፀም ያለበት ቢሆንም ከባድ አለመግባባት በስልጣን ክፍፍሉ ጉዳይ እንደተፈጠረ እየተገለፀ ነው፡፡ የኤምዲሲ ስራ አስፈፃሚ አባል ሳም ሲፔፓንኮም እንደሁም ምክትል ኘሬዚዳንቱ ቶኮዛኒ ኩፔ ለዓለም አቀፍ ሚዲያ እንደገለፁት ፓርቲያቸው በስራ አስፈፃሚው ወሳኝ ሥልጣን ካልተሰጣቸውና ሙጋቤ በይስሙላ ሥልጣን ብቻ ካልቀጠሉ ድርድሩን እንደማይቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ ተመድ የዳርፉር ተልዕኮ እንዲቀጥል ወሰነ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በችግር በታጠረችው የሱዳን ዳርፉር ግዛት ያሉት ሰላም አስከባሪዎች እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 15 አባላት ያሉት የፀጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ጥምር ሰላም አስከባሪ ካለፈው ሐሙስ ጀምሮ ለአንድ ዓመት ያህል ሥራውን እንዲቀጥል ድምፅ ሰጥቷል፡፡ አሜሪካ ድምፅ ያልሰጠች ስትሆን ውሳኔውን ተችታለች፡፡ ባለፈው ሐምሌ 15 የአፍሪካ ሕብረት በአልበሽር የዓለም አቀፍ ወንጀሎች ፍርድ ቤት መከሰስን የተቃወመ ሲሆን የዳርፉር የሰላም ሂደትን ይበጠብጣል የሚል ምክንያት ማቅረቡም ይታወሳል፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ የተባበሩት መንግሥታት አባል ሃገራት ለዳርፉር ሚሽን ሄሊኮኘተርን ጨምሮ አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያዋጡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም ሱዳን ለሚሽኑ ሙሉ ትብብር እንድታደርግ አሳስቧል፡፡ ሱዳን የአልበሽር ክስ ካልተነሳ ሰላም አስከባሪዎችን ከዳርፉር ለማባረር ዝታለች፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |