| ለዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራ... |
|
|
| Wednesday, 06 August 2008 | |
|
ለዘመናዊ ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራ የ282 ሚሊዮን ብር ስምምነት ተፈረመ
ከተማው ከአምስት ሳይቶች ለተሰሩት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ለገላን ቦሌ አያት ሳይት፣ ጆሞ፣ ጐተራና ጐፋ ለተባሉት የጋራ ቤቶች ሳይት የፍሳሽ ማስወገዳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና የፍሳሽ ማስወገጃ የማገናኘት ሥራ ኩባንያው እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡ (ኢዜአ) እናትና ልጅ በውሃ ተወስደው ሞቱ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እናትና ልጅ በደራሽ ውሃ ተወስደው መሞታቸውን የዞኑ ፖሊሲ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በእናትና ልጅ ላይ አደጋው የደረሰው እናት የቄሮ ገልፎ ወንዝን በመሻገር ከወንዙ ማዶ ከብት ይጠብቅ የነበረውን ልጃቸውን ለማምጣት በመሻገር ላይ እንዳሉ በድንገት በተከሰተ ደራሽ ውሃ ሲሆን፣ የአካባቢው ህብረተሰብ ከፖሊስ ጋር በመተባበር የሟቾቹን አስክሬን በመፈለግ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡ (አዲስ ዘመን ሐምሌ 28 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም". የእንቅርት በሽታ እናቶችንና ህፃናትን እያጠቃ ነው በቄለም ወለጋ ዞን በርካታ እናቶችና ሕፃናት በእንቅስር በሽታ እንደሚጠቁ ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡ የዞኑ ጤና መምሪያ በሽታውን ለመከላከል የበኩሉን ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ በሽታው በተለይ እናቶችና ሕፃናት ለእንቅርት በሽታ የሚጋለጡት ከጐረቤት ሀገር በህገ ወጥ መንገድ የሚገባውንና በአካባቢው የሚመረተውን አዮዲን የሌለው ጨው ስለሚጠቁሙ መሆኑን፣ በሽታው ጐልቶ የሚታየው በዞኑ አንፊሎና ጊዳሚ ወረዳዎች መሆኑን አስታውቋል፡፡ የዞኑ ጤና ጣቢያም ችግሩን ለማቃለል በተደረገው ጥረት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ138 ሺ ለሚበልጡ እናቶችና ሕፃናት የአዮዲ ካፕሱል ሕክምና መሰጠቱን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) በጐባና ሮቤ ሕገ ወጥ የነዳጅ ሽያጭ እየተካሄደ ነው በባሌ ዞን ለጐባሩ ሮቤ ከተማ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ሕገወጥ የነዳጅ ሽያጭ ላይ በመሰማራታቸው የትራንስፖርት ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ መጨመሩን የከተሞቹ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ማደያዎቹ መንደር ውስጥ በህገወጥ መንገድ ነዳጅ ለሚቸረችሩ ግለሰቦች፣ ነዳጅ በበርሜል ስለሚሸጡ፣ ነዳጅ ባራገፉ ማግስት ጨርሰናል ይላሉ፡፡ አንድ ሊትር ናፍጣ ከህገወጦቹ ቸርቻሪዎች በ13 ብር እንደሚገዙ ገልፀዋል፡፡ (ኢዜአ) የኔዘርላንድ መንግሥት ተጨማሪ እርዳታ ሰጠ የኔዘርላንድ መንግሥት በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች መርጃ የሚሆን ቀደም ብሎ ሰጥቶት ከነበረው 8.5 ሚሊዮን ዩሮ በተጨማሪ አምስት ሚሊዮን ዩሮ ሰጠ፡፡ እርዳታው ሙሉ በሙሉ ለሰብአዊ እርዳታው የሚውል መሆኑንና፣ ለምግብ ለህክምናና ለንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሚውል ተገልጿል፡፡ (ጋዜጣዊ መግለጫ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |