| ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ መሠረት ለመጣል |
|
|
| Sunday, 20 January 2008 | |
|
ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ መሠረት ለመጣል ለመንገድ፣ ለኃይል ማመንጫ፣ ለትምህርት ቤትና ለጤና ማዕከላት ግንባታ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትና የእርዳታ ድርጅቶች እገዛ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ሴክሬታሪ ልዩ አሜካሪና በኰሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአርዝ ኢኒስትትዩት ዳይሬክተር የሆኑት ኘሮፌሰር ጃፈሪ ሳች ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ የነበራቸውን የአምስት ቀናት ጉብኝት ሲጨረሱ በሰጡት መግለጫ፣ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይ ለማድረግ የገንዘብ እርዳታ ያስፈልጋታል፡፡ ለጋሾች ለአፍሪካ የሚሰጡትን እርዳታ በ2010 በእጥፍ ለማሳደግ ቢያቅዱም ተግባራዊ አለመሆኑን የገለፁት ኘሮፌሰር ሳችስ ኢትዮጵያ የጀመረቻቸውን የመሠረት ልማት ግንባታ ዳር ለማድረስ ቃላቸውን አክባሪ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ያስመዘገበችው ከአሥር በላይ የኢኮኖሚ እድገት ለሁለት አሥርት ዓመታት ቀጣይ የማድረግ አቅም እንዳላትም ተናግረዋል፡፡ የገበሬው የገቢ አቅም መዳበሩ አዳዲስና ምርታማ የሆኑ ግብአቶችን በመግዛት ምርታማነትም ሆነ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን የማሳደግ አቅም እንደሚፈጥርም ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ በከብቶች ኃብት፣ በማር፣ በቡና፣ በቱሪዝምና በኃይል ማመንጫ ሠፊ አቅም እንዳለባት ገልፀው የወጪ ባለሐብቶች በዘርፉ ያላቸውን እንቅስቃሴ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት የዓለም የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ነዳጅ ላኪ ካልሆኑ የአፍሪካ አገሮች ፈጣን የሚባለውን የ10.5 በመቶ የአገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት እድገት አስመዝግባለች፡፡ እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከደቡብ አፍሪካ 664 ቢሊዮን ዶላር ናይጄሪያ 197 ቢሊዮን ዶላር፣ ሱዳን 115 ቢሊዮን ዶላር በመከተል የ96 ቢሊዮን ዶላር ጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አስመዝግባለች፡፡ በዓለም የገንዘብ ድርጅት ስሌት መሠረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ወደ ኋላ የቀረ መሠረተ ልማት ሲኖራት የነፍስ ወከፍ ገቢው 1”123 የአሜሪካ ዶላር ብቻ መሆኑንም ያስረዳል፡፡ ከአፍሪካ አገሮች አነስተኛ የምርት እድገት ካስመዘገቡት አገሮች ዚምባቡዌ -6.2 በመቶ፣ ቶጐ 2.9 በመቶ፣ ቻድ 1.5 በመቶና ኤርትራ 1.3 በመቶ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |