| የሕብረት ሥራ ማኅበራት የራሳቸውን... |
|
| Sunday, 20 January 2008 | |
|
የሕብረት ሥራ ማኅበራት የራሳቸውን ባንክ እንዲያቋቁሙ ተመከሩ የሕብረት ሥራ ማህበራት ገበያ ውስጥ ሊያኖራቸው የሚችለውን የገንዘብ አቅም ለመፍጠር የራሳቸውን ባንክ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ በፌዴራል ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ወ/ሮ ይስገዱልሽ በዛብህ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የሕብረት ሥራ ማህበራት የሚቋቋሙት በራሳቸው በአባላቱ ተነሳሽነትና መዋጮ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ድርድር ውስጥ ገብተው ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ባለው ሂደት የመንግሥትና የግል ባንኮችን መመርኮዛቸው አቅማቸውን በብቃት እንደማያጎለብት ገልፀው፡፡ የሕብረት ሥራ ማህበራት ተሰባስበው የራሳቸውን ባንክ አቋቁመው ገበያ ውስጥ ሊያኖራቸው የሚችለውን የገንዘብ አቅም መፍጠር የተሻለ አማራጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የሚያቋቁሙት ባንክ ማህበራት በንግድና ልማት ባንክ ውስጥ ያለወለድ ያስቀመጡትን ገንዘብ ወደ ጋራ ንብረታቸው የሚያመጡበትን እድል እንደሚፈጥርም ተገል..ል፡፡ ገበያ ተኮር የአመራረትና የግብይት ዘዴ የተላበሱ ጠንካራና በነፃ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ለማጠናከር የካፒታል አቅማቸውን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ እንደ ወ/ሮ ይስገዱልሽ ገለፃ፣ የሕብረት ሥራ ማህበራትን አቅም ለማሳደግ በካፒታል፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ የመጋዘን የአሰራርና አመራር ሥርዐትና የግብይት ችግራቸውን በመፍታት የተጠናከረ እገዛ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የሕብረት ሥራ ማኅበራት ምርትና አገልግሎት ባልሠለጠነ የሰው ኃይልና አነስተኛ ቴክኖሎጂ የተመሰረተ መሆኑ ለመንግሥት ድጋፍ ጥገኛ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ገልፀው፡፡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅማቸውን ለማሳደግ ያሉት ጅምሮች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም ተጠቁሟል፡፡ በግብይት ምርትን የማሰባሰብ፣ የግዢ፣ የጥራት፣ የደረጃ፣ የማሸግ የማከማቸት ጥራትን የማቀነባበር፣ የማስተዋወቅ፣ የግብይት ተመንና የምርት አቀራረብ ተግባራት የሚያጠቃለል የግብይት አቅም ማነስ እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡ በበቂ ሁኔታ የማምረት ችግር እንዳለባቸውና በግል ንግድ ከተሰማሩት ጋር ተወዳዳሪ የሆነ አቅም ለመገንባት ምርታማነት በሚጨምርበት ሂደት በርካታ ሥራ በፌዴራልና በክልል ኤጀንሲዎች መሰራት እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡ አምራቾች የአትክልትና የፍራፍሬ ምርቶቻቸውን ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ወደ ማዕከል ገበያ አምጥተው እንዳይሸጡ የማቀዝቀዣና የትራንስፖርት ችግር ትርፋማነታቸውን እንደሚፈታተናቸውም ገልፀዋል፡፡ የምርት አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር በማጣጣም አምራችና ሸማቹ ትስስር በመፍጠርና የቅብብሎሽ ሂደትን በማሳጠር በወቅታዊ ሁኔታ ተሰቅሎ የሚቀረውን ዋጋ ከገበያ ሁኔታ ጋር በማስተካከል የሚኖራቸው ሚና ጉልህ መሆኑም ተመልክቷል፡፡ የሸማቾች ሕብረት ሥራ ማህበራት በተበታተነና አብዛኛውን ሸማች ባላቀፉበት ሁኔታ እየሰሩ ቢሆንም በሸቀጦች ዋጋ መናርና የጥራት ጉድለትን ለመከላከል አመቺ ሁኔታ የመፍጠር አቅም እንዳላቸውና የሕብረት ሥራ ማህበራት ጋር በትስስር መስራት እንደሚገባቸው አመልክተዋል፡፡ የሕብረት ሥራ ማህበራትን ለማስፋፋት ተገቢውን ጥረት የማድረግ፣ ስልጠናዎችና ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ፕሮግራሞችን የመቅረፅ፣ አስፈላጊ የአደረጃጀት መመሪያዎችን ማዘጋጀት የአደረጃጀት መምሪያና ተሞክሮችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑም ተገል..ል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አሽጎ አቀነባብሮ ለሸማቹ በሚመች መልኩ የሚያቀርቡት በቡና፣ በወተት ተዋፅኦ ላይ የተሰማሩት ማህበራት ሲሆኑ በሌሎች ዘርፎች ላይ በትኩረት ሊሰራባቸው፡፡ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ በብዛት፣ በጥራትና በጊዜ የማምረት አቅጣጫን በመከተል ምርታማነትን ለማሳደግ ወጪ ቆጣቢና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከሰለጠነ የሰው ኃይል አጣምሮ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን አብራርተው አሁን በ6 የከፍተኛ ተቋማት በዲግሪ ፕሮግራም ባለሙያዎች ቢሰለጥኑም በበቂ ሁኔታ ያልተመለሰ ጥያቄ በመሆኑ በተጠናከረ መልኩ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱም ጥሬ ምርት አቅራቢ ከመሆን ያለቀ ወይም በከፊል የተዘጋጀ ምርትን ለማቅረብ በመዘጋጀት በብሔራዊ አሁጉራዊ ገበያ ውስጥ ለመግባት የሚያስችላቸው የገበያ ትስስር መፍጠር እንደሚገባቸውም ተገል..ል፡፡ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በሁለተኛ የአደረጃጀት ደረጃ መደራጀት ከተጀመረበት 1989 ዓ.ም ጀምሮ 2,909 መሰረታዊ የሕብረት ሥራ ማህበራት አባላት ያሏቸው የሕብረት ሥራ ዩኒየኖች ተደራጅተው 136.9 ሚሊዮን በላይ ካፒታል እንዳላቸው ከኤጄንሲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የኅብረት ሥራ ከ21 በላይ የሕብረት ሥራ ማህበራት አይነቶች ከ19..147 የሕብረት ሥራ ማህበራት እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ከ4 ሚሊዮን በላይ አባላትና 1.4 ቢሊየን በላይ ካፒታል አላቸው ይህ በአገሪቱ ውስጥ ከሚኖረው አባወራ 27.3 በመቶ ብቻ በሕብረት ሥራ መደራጀታቸውን ያመላክታል፡፡ በቤዛዊት ሥዩም |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |