Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow የሆላንድ ካር ባለቤት አዲስ የፒካፕና...
የሆላንድ ካር ባለቤት አዲስ የፒካፕና... Print E-mail
Sunday, 20 January 2008

የሆላንድ ካር ባለቤት አዲስ የፒካፕና የሚኒባስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሊገነቡ ነው

ሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግ.ማ በሚል መጠሪያ በሆላንድ ኩባንያና በአንድ ኢትዮጵያዊ የቤት አውቶሞቢሎችን በመገጣጠም ሥራ የጀመረው ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ባለንብረት አዲስ የፒካፕና ፎርዊልድራቭ ሚኒባሶች መገጣጠሚያ ፋብሪካ አቋቋመ፡፡

በሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግ.ማ ውስጥ በስራ አስኪያጅና በኩባንያው አንደኛው ባለድርሻ በሆኑት ኢንጂነር ታደሰ ካስዩፒያ ካር ኃ.የተ.የግ.ማ የሚል መጠሪያ የተሰጠውን የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ያቋቋሙት ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር በመሆን ነው፡፡

ኢንጂነር ታደሰ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለቤትነት የሚተዳደር ፋብሪካ ለማቋቋም ባላቸው ፍላጎት መሰረት ከሆላንድ ካር ኃ.የተ.የግ ማህበር ኩባንያ ጎን ለጎን ይህንን አዲስ የፒካፕና የሚኒባስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ማቋቋማቸውን ይገልፃሉ፡፡

በ30 ሚሊዮን ብር የተቋቋመው አዲሱ ኩባንያ በአመት አንድ ሺህ ሚኒባሶችና ፒካፖችን ለማምረት የሚችል ሲሆን በኩባንያው የሚገጣጠሙት ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ የሚሆነውን ማሽነሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት ጎና ከተባለ የቻይና ኩባንያ የሚያስመጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከቻይና ኩባንያ ጋርም ማሽነሪዎቹን ለማቅረብ የመኪና አካላቱን ግዥ በሚመለከት ከስምምነት ላይ በመደረሱ በመጪው መስከረም የመጀመሪያዎቹ ተሽከርካሪዎች ለገበያ እንደሚቀርቡ አመልክተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማግኘታቸውን የገለጹት ኢንጅነር ታደሰ ፋብሪካው የሚገነባበትን ቦታም በቅርቡ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡

በሆላንድ ካር ውስጥ ያላቸው ድርሻ እና ሃላፊነት እንዳለ የሚቆይና በአዲሱ ኩባንያቸው ከሚመረቱት ተሽከርካሪዎች ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው መሆኑ አስታውቋል፡፡

በሁለቱ ተመሣሣይ ኩባንያዎች ውስጥ መስራቱም ችግር እንደማይፈጥር ተገል”ል፡፡

ሆላንድ ካር ኦክ እና አባይ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸውን ሁለት ተሽከርካሪዎች ገጣጥሞ ለገበያ ያቀረበ ሲሆን በቀጣይነትም ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም በዝግጅት ላይ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ካስፒያ የተባለውን ኩባንያ በዋናነት ፒካፕ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት የተቋቋመ ቢሆንም በሆላንድ ካር ሊመረት የታቀደውም ፒካፕ ተሽከርካሪ በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንደሚመረት ገልፀዋል፡፡

ሆላንድ ካር በሆላንድ መንግሥት ድጋፍ በማግኘት ትውንታ ከተባለ የሆላንድ ኩባንያና ኢንጅነር ታደሰ በጋራ ያቋቋሙት ኩባንያ ሲሆን አባይ የሚል መጠሪያ የተሰጣትን የቤት አውቶሞቢል ለማምረት ሲባል አንድ የቻይና ኩባንያ ከሆላንድ ካር ጋር በጥምረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በሆላንድ ካር በቀጣይ ትመጣለች ተብሎ የምትጠበቀው ፒካፕ ተሽከርካሪ አዋሽ የሚል ስያሜ እንደተሰጣት መገለፁ ይታወሳል፡፡  

በዳዊት ታዬ

 
< Prev   Next >