| በኬንያ የምርጫ ውዝግብ... |
|
|
| Sunday, 20 January 2008 | |
|
በኬንያ የምርጫ ውዝግብ አልበረደም የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ የኬንያ ኘሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ የዳግም ምርጫ ጥያቄን እንዲቀበሉ ጫና ለመፍጠር የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲው፤ ከመንግሥት የንግድ ተቋማት የሚመረቱትን ምርቶች እንዳይገዙ ለደጋፊዎቹ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የኬንያ ፖሊስ በበኩሉ ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰዎችን ለዓመፅ እያነሳሱ ነው ሲል ወንጅሏል፡፡ በኬንያ የኘሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤትን ተከትሎ በተነሳ ግጭት ከስድስት መቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከሁለት መቶ ሀምሳ ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡ ተመድ ለአልጄሪያ ጥያቄ አቀረበ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአልጄሪያ ውስጥ የተደረገውን የድርጅቱን ሠራተኞች ግድያ በተመለከተ የአልጄሪያ መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በድጋሚ ጥያቄ ማቅረቡን ቢቢሲ ከስፍራው ዘገበ፡፡ የተመድ የልማት ኘሮግራም ተጠሪ ከማል ደርቪስ "ለአልጄሪያ መንግሥት ያቀረብነው ጥያቄ ምላሽ አጥቷል" ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የተመድ ባለሥልጣናት ያለፈው ወር በአልጄሪያ አሥራ ሰባት የድርጅቱ ሰራተኞች ላይ የተፈፀመው ግድያ እንዲጣራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአልጄሪያ መንግሥት ለጥያቄው መልካም ምላሽ አለመስጠቱ ተዘግቧል፡፡ የቢንላደን ልጅ "ለሠላም አምባሳደርነት" የቢንላደን ልጅ ኦማር ኦሳማ ቢንላደን እስልምናን ለመጠበቅ ከመሳሪያ የተሻለ መንገድ መኖሩንና የሠላም አምባሳደር ሆኖ መሥራት ይፈልጋል ሲል አሶሺየትድ ኘሬስ ዘገበ፡፡ የ26 ዓመቱ ኦማር የቢንላደን 19ኛው ልጅ ሲሆን ባለፈው ዓመት ከ52 ዓመቷ እንግሊዛዊት ጃኒ ሬሊክስ ጋር ጋብቻ ሲፈፅም የበርካታ ጋዜጦችን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ "የምዕራባዊያኑን አስተሳሰብ ለመለወጥ ነው፡፡ በርካታ ሰዎች አረቦች በተለይም የቢንላደን ልጆች ሁሉ አሸባሪዎች ይመስሏቸዋል፡፡ ይኸ ግን እውነት አይደለም" ይላል ኦማር፡፡ ከጋብቻ በኋላ ስሟን የለወጠችው ባለቤቱ ዚያና አልሳባህ ኦማር ለመስማት የሚፈልግና "በዓለም ላይ ካሉ ሰዎች ይኸን ማድረግ የሚችል ብቸኛው ሰው ነው" ብላለች፡፡ ካስትሮ ለመናገር አቅም አጥተዋል የኩባው ፊደል ካስትሮ ለህዝቡ ንግግር ለማድረግ ጤናቸው እንደማይፈቅድላቸውና ዛሬ ለሚደረገው የፓርላማ ምርጫ መቅረብ እንደማይችሉ ገለፁ፡፡ የ81 ዓመቱ ኘሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ በፖለቲካ መሪነታቸው ለመቀጠል ጤንነታቸው እንደሚፈቅድ የብራዚሉ ኘሬዚዳንት ከተናገሩ በኋላ የተላለፈው የካስትሮ አስተያየት ጤንነታቸው እንዳልተሻሻለ የሚጠቁም ተደርጎ ተወስዷል ሲል የሀገሪቱ የዜና አገልግሎት ተቋም ያወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |