Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያና ዓለም ባንክ...
ኢትዮጵያና ዓለም ባንክ... Print E-mail
Sunday, 20 January 2008

ኢትዮጵያና ዓለም ባንክ የ256 ሚሊዮን ዶላር ሥምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ባንክ የ256 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብድርና እርዳታ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ከገንዘቡ ውስጥ 215 ሚሊዮን የሚሆነው ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ለመሠረታዊ አገልግሎት ኘሮግራም እንደሚውል፣ በክልል መንግሥታት የትምህርት፣ የእርሻ፣ የውኃ፣ የጤና ዘርፍ የልማት ግብን ለማሳካት፣ የመንግሥትን ገንዘብ ግልፅነትና ተጠያቂነት ለማጠናከርና ለአቅም ግንባታ ሥራዎች ለማካሄድ እንደሚውል ተጠቁሟል፡፡

(አዲስ ዘመን ጥር 9 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም)

የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጆች ፀደቁ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት፣ በዓለም አቀፍ የልማት ማህበርና በዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ፣ መካከል የተደረጉትን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጆች አፀደቀ፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገው የ65 ሚሊዮን 6ዐዐ ሺ ዶላር የብድር ስምምነት መሆኑን፣ ብድሩ በሰሜን ጐንደር በጣና ዙሪያ 2ዐ ሺ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት የተያዘውን ኘሮጀክት ለማስፈፀም የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ኢዜአ)

ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር አገልግሎት ተጠሰ

ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ከአንድ ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ለሚበልጡ ስዎች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የምክር አገልግሎት መስጠቱን ገለፁ፡፡

በአዲሱ ሚሊኒየም አገሪቱ የተያያዘችውን የፀረ ኤድስ ዘመቻ ከግብ ለማድረስ ከአንድ ሺ በላይ የሚሆኑ የአገልግሎት መሸጫ ጣቢያዎች አማካኝነት የምክር አገልግሎት ለመስጠት መቻሉን ገልጿል፡፡

(ዋኢማ)

የሉሲ ቅሪተ አካል ከ1ዐዐ ሺ በሚበልጡ ሰዎች ተጐበኘ

በቴክሳስ ግዛት በሚገኘው የሂውስተን የፈጥሮ ሣይንስ ሙዚየም ለዕይታ የቀረቡት የሉሲ ቅሪትና የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቅርሶች ከ1ዐዐ ሺ በሚበልጡ ቱሪስቶች እየተጐበኙ መሆናቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

በሙዚየሙ ታሪክ ከተጐበኙት የአሜሪካ የሌሎች አገሮች ቅርሶች ውስጥ የሉሲ ከፍተኛ ተመልካች ማግኘቱንና ወደ ሌላ ግዛት ከመሄዱ በፊት ከመጋቢት እስከ ሰኔ ወር የሚቆየው የሂውስተን ዓመታዊ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ለእይታ እንደሚቀርብ አመልክቷል፡፡

(ኢዜአ)

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር በ40 ሚሊዮን ዩሮ ሊታደስ ነው

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር በ40 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ እንደሚጠገን የጅቡቲ አምባሳደር በኢትዮጵያ ተናገሩ፡፡

ከአውሮፓ ዩኒየን በተሰጠው ገንዘብ ሊሰራ የታሰበው የባቡር ሀዲድ ዝግጅቱ ተጠናቆ ሥራውን ለመጀመር ከታወቀ የኩዌት ኩባንያ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አምባሳደሩ ገልፀዋል፡፡

(ዘ ኢትዮጵያን ሄራልድ ጥር 8 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም)

 
< Prev   Next >