| አህመድ ያሲን መንግሥት ለችግራችን... |
|
| Sunday, 28 September 2008 | |
|
አህመድ ያሲን መንግሥት ለችግራችን መፍትሄ ይፈልግልን አሉ
በደረጀ ጠገናው በፊፋ ዕውቅና የተነፈገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቀድሞ አመራር ጋር የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ጥሪ አቀረበ፡፡ አቶ አህመድ ያሲን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት በተለይ ለሪፖርተር ጋዜጣ ዓርብ ዕለት በጽ/ቤታቸው በሠጡት ቃለምልልስ እንዳስታወቁት በፌዴሬሽኑ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረው ችግር የአገር ጉዳይ መሆኑን፣ ችግሩ ለእግር ኳስ ዕድገት አሉታዊ ተፅዕኖ ከማስከተሉ በተጨማሪ የአገሪቱ አንጡራ ሀብት ለብክነት እየዳረገ በመሆኑ መንግሥት በጉዳዩ ገብቶ ፖለቲካዊ ውሣኔ ሊሰጥበት ይገባል፡፡ መንግሥት ይግባ ሲባል መንግሥት በስፖርቱ ውስጥ ጣልቃ ይግባ ማለታችን አይደለም የሚሉት አቶ አህመድ ለብሔራዊ ጥቅም ሲባል በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር የተጣለብንን ቅጣት ለመቀልበስ በሕጋዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ የምናደርገው ትግል እንደተጠበቀ ሆኖ መንግሥት የገጠመንን ችግር ዝም ማለት አይገባውም ብለዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የፊፋ እገዳ በመቃወም ችሎታ ያላቸው ጠበቃ ቀጥሮ ጉዳዩን ወደዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍ/ቤት (ካስ) መውሰዱንም አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡ (ከአቶ አህመድ ጋር የተደረገው ቃለምልልስ በረቡዕ ዕትማችን ይስተናገዳል)፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |