| "የትኛውም የአፍሪካ አገር የሚሊኒየሙን... |
|
| Sunday, 28 September 2008 | |
|
"የትኛውም የአፍሪካ አገር የሚሊኒየሙን ግቦች ሙሉ ለሙሉ አያሳካም" ባንኪሙን
በጋዜጣው ሪፖርተር “ከማንም የበለጠ ጠንቅቃችሁ እንደምታውቁት ወቅታዊ ሁኔታዎች የትኛውም የአፍሪካ አገር የሚሊንየሙን የልማት ጐሎች ሙሉ ለሙሉ አያሳካም” ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ሚ/ር ባንኪሙን በ63ኛው ጠቅላላ የድርጅቱ ስብሰባ ላይ ገልፀዋል፡፡ ድህነትን ለማስወገድ የተነደፈ ስምንት ዋና ዋና የልማት ግቦችን በመቅረፅ እ.ኤ.አ እስከ 2ዐ15 ለማሳካት የታለመ ቢሆንም በዓለም ላይ በዋናነት በአፍሪካ የሚታየው እወነታ አስቸጋሪ ነው፡፡ ዋና ፀሐፊ ባንኪሙን የልማት ግቦቹን ለማሳካት በዓመት 72 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ገንዘብ ድጋፍ የሚያስፈልግ መሆኑን አውስተው ባለፈው ዓመት ከ267 ቢሊዮን ዶላር በላይ በኢኮኖሚና ልማት ትብብር ድርጅት በኩል ወጪ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ ባንኪሙን አፅንኦት በሰጡት ንግግራቸው የዓለም መሪዎች በፀና አቋምና ቁርጠኝነት ታሪክን ለመለወጥ መሥራት አለብን ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል የአፍሪካ መሪዎች በዓለም የተከሰተው የፋይናንስ ቀውስ የተመድ ግቦችን ሊያደናቅፍ እንደማይገባ ገልፀዋል፡፡፡ መሪዎቹ እንዳስገነዘቡት በበለፀጉ አገሮች ላይ የተከሰተው ቀውስ እርዳታ ለመስጠት የተገባውን ቃል ለማስተጓጐል እንደ ምክንያት ሊወሰድ አይገባም፡፡ ቃል የተገባባቸው በርካታ እርዳታዎች እየቀነሱ ባለበት ወቅት የገንዘብ ቀውሱ መከሰት የተመድ ልማት ግቦችን እንዳይሳኩና ደህነትንም ለመቀነስ ፈታኝ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ በአፍሪካ የተመድ ግቦተን ለማሳካት ባንኪሙን እንዳሉት በዓመት 72 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ማድረግ የሚቻልበት ተስፋ እየተሟጠጠ ያለበት ሁኔታ ይታያል፡፡ በዓለም የተፈጥሮ አደጋዎች የዋጋ ንረት፣ የእርስ በርስ ግጭቶች፣ የገንዘብ ቀውስና ሌሎችም ተደማምረው ድሃ አገሮችን ከድህነት ለማላቀቅ የተያዘውን ግብ በእንጥልጥል አስቀርተውታል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |