Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የልብ በሽታ ፈጣን የሞት...
የልብ በሽታ ፈጣን የሞት... E-mail
Sunday, 28 September 2008

የልብ በሽታ ፈጣን የሞት መንስኤ እየሆነ ነው

የልብ በሽታ ባደጉት አገሮች ቁጥር አንድ ገዳይ ከመሆኑም በላይ በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮችም ፈጣን የሆነ የሞት መንስኤ እየሆነ መምጣቱን አዲስ የልብ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡

 

እስካሁን በተገኘው መረጃ የልብ በሽታ ህሙማን ቁጥር ከሰሀራ በታች በሚገኙ አገሮች እድገቱ እየጨመረ መሆኑን፣ በበለጸጉት አገሮች ከሚከሰቱ ሞቶች 50 በመቶ የሚሆነው ልብና ልብ ነክ በሆኑ ቦታዎች መሆኑን፣ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች አሀዙ ከ35 ዓመት በላይ መሆኑን ገል"ል፡፡
(ኢዜአ)


ከበልግ ምርት 497 ሺህ ኩንታል በላይ እህል ተገኘ

በባሌ ዞን ጋሠራ ወረዳ ከ2000 ዓ.ም የበልግ ምርት 497ሺህ ኩንታል በላይ መገኘቱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ገለፀ፡፡

የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በ2000 የበልግ ወቅት ከ22ሺ 378 ሄክታር መሆኑ ላይ ከተዘሩት ከተለያዩ የእህል ዘር 497 ሺህ 197 ኩንታል ምርት መገኘቱን፣ ካለፈው በጀት ዓመት ምርት ጋር ሲነፃፀር 36 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተገል"ል፡፡
(የኦሮሚያ ማስታወቂያና ሕዝብ ግንኙነት ቢሮ)

ለአርብቶ አደር ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ 70 ሚሊዮን ብር ተመደበ

በአፋር ክልል በዚህ ዓመት ለሚከናወኑ የአርብቶ አደር ልማት ፕሮጄክቶች ማስፈፀሚያ 170 ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡን የክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

በበጀቱ በግብርና፣ በውሃ ሀብት፣ በገጠር መንገዶች በጤና፣ በትምህርትና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ያተኮሩ ፕሮጄክቶች እንደሚከናወኑ፣ በግብርና ዘርፍ የሚካሄዱት አስር ፕሮጀክቶች በገበያ መረጃ፣ በእንስሳት ጤና አገልግሎት ላይ እንደሚያተኩሩ፣ ዘጠኝ ድርጅቶች በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና በሳኒቴሺን ዘርፎች ላይ እንደሚያተኩሩ አስታውቋል፡፡
(አዲስ ዘመን መስከረም 15 ቀን 2001 ዓ.ም)

ከ100ሺህ ሄክታር የሚበልጥ ኮትቻ አፈር እየለማ ነው


በደቡብ ወሎ ከ100ሺህ ሄክታር የሚበልጥ ኮትቻ አፈርን በማጠንፈፍ ምርታማ ማድረግ መቻሉን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በዘንድሮው መኸር ኮትቻ መሬትን ጨምሮ 462ሺህ 344 ሄክታር መሬት በልዩ ልዩ ሰብል መሸፈኑን፣ ቢቢኤም በተባለ የእርሻ መሣሪያና አርሶ አደሩ ባደረገው ባህላዊ የኮትቻ መሬት የማጠንፈፍ ዘዴ በመጠቀም ቀደም ሲል ይገኝ የነበረውን ምርት በሶስትና አራት እጥፍ ማሳደግ መቻሉን ገል"ል፡፡
 (ኢዜአ)

ተሽከርካሪዎች በየመንገድ ዳር ለመቆም መገደዳቸውን ገለጹ

በምዕራብ ወለት ጊምቢ ከተማ የአውቶቡስ መናኸሪያ ባለመኖሩ በየመንገዱ ግራና ቀኝ የሚቆሙ በርካታ ተሽከርካሪዎች በእግረኛም ሆነ በትራፊክ እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን የከተማው ነዋሪዎች አመለከቱ፡፡

በመንገዱ ግራና ቀኝ ቆመው የሚያስተናገዱ የሕዝብ ማመላለሻዎችም ከሚያደርሱት መጨናነቅ በተጨማሪ በተጓዦች ላይ የሚፈፅሙት ሕገወጥ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
(ኢዜአ)
 
< Prev   Next >