Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ወል ማርት ለሠራተኞቹ ካሳ...
ወል ማርት ለሠራተኞቹ ካሳ... E-mail
Sunday, 28 September 2008

ወል ማርት ለሠራተኞቹ ካሳ እንዲከፍል ተፈረደበት

ግዙፉ ኩባንያ ወል ማርት ለሠራተኞቹ መክፈል የሚገባውን የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ክፍያና ሊያገኙት የሚገባውን በቂ እረፍት በመከልከሉ ከወራት በፊት የሚኒሶታ ፍርድ ቤት 6.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ የፈረደ ሲሆን ወል ማርት ጉዳዩን ወደ ማሳቹሴት ከፍተኛው ፍርድ ቤት በይግባኝ ይዞት ሄዶ ፍርዱ እንደፀናበት አሜሪካን ሎውዬር ዘግቧል፡፡

 

እ.ኤ.አ በ2006 በታችኛው ፍርድ ቤት የተጀመረው ክርክር 67500 የአሁንና የቀድሞ የወል ማርት ሠራተኞችን የቡድን ጥያቄ የተመለከተ ነው፡፡ በ2ዐዐ6 ወል ማርት በከፊል ክሶቹን ማስተባበል የቻለ ቢሆንም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛው ቶማስ ሙርታጁ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በማለት ውሳኔውን ቀልብሷል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የስር ፍርድ ቤቱ ዳኛ ሙርታጅ ከሳሾቹ ያቀረቡትን ዋነኛ ልዩ አዋቂ ምስክር የማያስተማምን ምስክር በማለት ማግለላቸውን ተችቷል፡፡ ወል ማርት ባለፈው ማክሰኞ በድጋሚ ይግባኝ ሲልም በድጋሜ ፍርዱ ፀንቷል፡፡

ዘገባው የሠራተኞቹ ጠበቃ ሮበርት ቦንሲግኖር "ክልሎች ጉዳያቸውን ራሳቸው መፈፀም አለባቸው፡፡ በይግባኝ ብዙ ጊዜ ማባከን አይኖርብንም" ማለቱን አመልክቷል፡፡ የማሳቹሴቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለውጥ አለማድረጉ አስተያየቱን ትክክለኛ እንደሚያደርገውም አሜሪካን ሌውዬር አስነብቧል፡፡
 
< Prev   Next >