Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Thursday
Jan 08th
Home arrow Sections arrow የናሚቢያ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ...
የናሚቢያ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ... E-mail
Sunday, 28 September 2008

የናሚቢያ የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ሥርዓት ሕግ ትችት እያስተናገደ ነው

በናሚቢያ ዊንድሆክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማጭበርበር ወንጀል የተከሰሰ የስዊዘርላንድ ዜጋ በሃገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ሁለት ክፍሎች ላይ የሰላ ትችት መሰንዘሩን ዘ ናሚቢያን ከወደዊንድሆክ ዘግቧል፡፡

 

የ62 ዓመቱ ሀንስ ፒተር ሮተን በናሚቢያ መደበኛ ነዋሪ ሲሆን ትችት የሰነዘረበት የህግ ክፍል አስቀድሞ በጎረቤት ሀገር ደቡብ አፍሪካ ኢ ሕገ መንግሥታዊ ነው ተብሎ ውድቅ የተደረገ ነው፡፡

ሮተን ነገ የክስ መሰማት ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ አመልክቷል፡፡ የደቡብ አፍሪካው ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ሁለት ክፍሎች ኢ ሕገ መንግሥታዊ ናቸው ብሎ የወሰነው በአግባቡ የመዳኘት መብትንና ንፁሕ ሆኖ የመታሰብን መብት ይጣረዛሉ በማለት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1977 የወጣው ሕግ በ2ዐዐ4 በፓርላማ አዲስ ሕግ በረቂቅም እስከአሁን ተፈፃሚ አልሆነም፡፡ የ1977ቱ ሕግ ክፍል 245 እና 322"5) በማጭበርበር ወንጀል ተጠርጣሪው በሀሰት ጉዳዩን እንደፈፀመ በድርጅት ጉዳይ ደግሞ ሥራ አስኪያጁና ሠራተኞቹ ሌላ ማስረጃ ከሌለ እንደተሳተፉበት ታሳቢ ያደርጋል፡፡

ተጭበርብሯል የተባለው ገንዘብ የናሚቢያ 1093 ሚሊዮን ብር ሲሆን ሮተን የዋስትና መብቱ ተከብሮለት በውጭ እየተከራከረ ይገኛል፡፡
 
< Prev   Next >