| የኬንያ አቃቤ ሕጎች ፖሊሷን ከሰሱ |
|
| Sunday, 28 September 2008 | |
|
የኬንያውን ፈላጭ ቆራጭ ቶማስ ቾልሞንዴሌይን ከተከሰሰበት የሰው መግደል ወንጀል ነፃ ሊያወጣው የሚችልን መረጃ መርማሪ ፖሊሶች እንዳጠፉ የተጠርጣሪው ጠበቃ መግለፁን ዴይሊ ቴሌግራፍ ዘግቧል፡፡
ጠበቃው ፍሬድ ኦጂያምቦ ለናይሮቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደተናገረው ተገደለ የተባለበትን የጥይት ቀለሀ ፖሊሶች በማጥፋት ቾልሞንዴሌይ አለመተኮሱን እንዳያረጋግጥ አድርገውታል፡፡ ተጠርጣሪው ሮበርት ንጆያ የተባለን ግለሰብ ገድሏል ተብሎ ክስ የቀረበበት ቢሆንም ጠበቃው ግለሰቡ በተገደለበት ወቅት ከተጠርጣሪው ጋር አብሮ የነበረው ጓደኛው ካርል ቱንዶ ግድያውን እንደፈፀመ ለማረጋገጥ ሞክሯል፡፡ የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከዘር ጋር የተያያዙ ውጥረት የበዛባቸው ጉዳዮችን በመስማት ላይ ሲገኝ ብዙዎቹ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ጋር የተያያዙ ተጠቃሚ ነጮችንና ጥቁር ደሀዎችን ክርክር የተመለከቱ ናቸው፡፡ የአሁኑ ተጠርጣሪ ቾልሞንዴሌይ ቤተሰብ ተጠቃሚ ከሚባሉ ነጮች ቅድሚያውን ይይዛል፡፡ የክስ መሰማቱ ሂደት ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ አቃቤ ሕጎች ፖሊስ መዋሸቱን ተናግረዋል፡፡ የመጨረሻ ውሳኔ በመጪው ጥቅምት ወር መጨረሻ ይጠበቃል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |