| ዘጎድ ፋዘር "ምርጥ ፊልም" ተሰኘ |
|
| Sunday, 28 September 2008 | |
|
በማፍያ ፊልምነት የሚታወቀው ዘጎድ ፋዘር የምንግዜም ታላቅ ፊልም በመሰኘት መመረጡን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
ከ10"000 በላይ የሲኒማ ተመለካቾች፣ ፊልም ሰሪዎችና ሐያስያን በሰጡት ድምፅ ነው፡፡ ዘጎድ ፋዘር ብልጫውን ያገኘው፡፡ የ1972 ፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ ፊልም ማርሎን ብራንዶ እና አል ፓቺኖ የተወኑበት ፊልም ነው፡፡ በደረጃው ሰንጠረዥ "ሬይደርስ ኦፍ ዘ ሎስት አርክ" እና "ዘኢምፓየር ስትራይክስ ባክ" ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነዋል፡፡ ከዳይሬክተሮች ኬንቲን ታራንቱኖ እና ማይክ ሌግህ ከደረጃው ሰንጠረዥ ይገኙበታል፡፡ በ21ኛው ምዕት ዓመት ከተሠሩት ፊልሞች ከምርጥ 20 ውስጥ የገቡት "ዘሌተስት ባትማን ፊልም"ና "ዘዳርክ ናይት" ሲሆኑ፣ "ዘሎርድ ኦፍ ዘሪንግስ" ከ60ዎቹ ውስጥ ተካትቷል፡፡ በ500 ዝርዝር ውስጥ "ኢዚ ራይደር"፣ "ዘሳውንድ ኦፍ ሚዩዚክ"ና የኦስካር አሸናፊው "ሼክስፒር ኢን ላቭ" አለመግባታቸው አስገራሚ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ከእንግሊዝ ሁለት ፊልሞች በ100 ዝርዝር ውስጥ የገቡት "ኤ ክሎክወርክ ኦሬንጅ" (37ኛ"፣ "ካዚኖ ሮያሌ" (56ኛ) ሆነዋል፡፡ የጀምስ ቦንድ "ጎልድ ፈንገር" ፊልም በዝርዝሩ ውስጥ ይገኛል፡፡ "ሐሪ ፖተር" እና "ዘፕሪዝነር ኦፍ አዝካባን" 471ኛው ተራ ላይ ተመዝግበዋል፡፡ 10"000 ሲኒማ ተመልካቾች፣ 150 የሆሊውድ ዳይሬክተሮችና 50 የፊልም ሐያስያን በምርጫው መሳተፋቸው ታውቋል፡፡ "ዘጎድ ፋዘር" በአማርኛ "የጡት አባት" ተብሎ መታተሙ ይታወሳል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |