Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow አሜሪካ ለኢኳዶር ቅርሶችን መለሰች
አሜሪካ ለኢኳዶር ቅርሶችን መለሰች E-mail
Sunday, 28 September 2008

Imageየአሜሪካ ባለስልጣኖች "ቅድመ ኮሎምቢያን" ተብለው የሚታወቁ የእጅ ጥበብ ውጤቶች ለኢኳዶር መመለሷን ኤፒ ዘገበ፡፡

 

የተሰረቁ ባህላዊ ቅርሶችን ወደ ትውልድ አገራቸው የመመለስ ስምምነትን ተግባራዊ በማድረጓም መላሿ ውዳሴ አግኝታበታለች፡

በእጅ ጥበብ የተሰሩት ሸክላዎች፣ ቅርጫቶች፣ ጌጣጌጦችና ቅርጻ ቅርጾች ብዛታቸው 168 ሲሆን፣ የተሰበሰቡትም ከሚያሚ ነው፡፡ ቅርሶቹ ክርስቶፈር ኮሎምቦስ አሜሪካ ከመድረሱ በፊት የተገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ "ቅርስን ወደነበረበት መመለስ፣ ታሪክን መመለስ ነው" በማለት የአሜሪካን እርምጃ ያወደሱት በሚያሚ የኢኳዶር ዋና ቆንሲላ ጅዋን ካርሎስ ቶሌዶ በሰሜን ሚያሚ ቢች በተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ላይ ነበር፡፡

ባለሙያዎች እንደተናገሩት ቅርሶቹ ከ2"000 እስከ 5"000 ዓመታት እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ቅርሶች ለአማልክቱ መስዋዕት ማቅረቢያ ሆነው ያገለግሉ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

ቅርሶቹ ወደ ኢኳዶር በመጓዝ በደቡብ አሜሪካዋ ከተማ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በሙዚየም እንደሚቀመጡ ታውቋል፡፡
Last Updated ( Sunday, 28 September 2008 )
 
< Prev   Next >