Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የዓለም ቱሪዝም ቀን - መስከረም 17
የዓለም ቱሪዝም ቀን - መስከረም 17 E-mail
Sunday, 28 September 2008

በሔኖክ ያሬድ

በየዓመቱ መስከረም 17 ቀን (ሴፕተምበር 27) በመላው ዓለም የሚከበረው የዓለም ቱሪዝም ቀን በኢትዮጵያ ከትናንት ጀምሮ በመከበር ላይ ነው፡፡ በዓለም ለ29ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው በዓል መሪ ሐሳቡ "ቱሪዝም - ለፈታኙ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ያበረክታል" የሚል ነው፡፡

 

ዓመታዊው በዓል መጀመሩ በተበሰረበት መስከረም 13 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ታደለች ዳለቾ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የበርካታ ብዝሐ ሕይወት፣ ሥነ ምድራዊ ገጽታዎችና የተፈጥሮ ሀብቶች ባለቤት መሆኗ ለቱሪዝም መዳረሻነት ምቹ ያደርጋታል፡፡

ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው ብርቅዬ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች በተጨማሪ በኢኮቱሪዝም፣ በአግሮ ቱሪዝምና ሐይድሮ ቱሪዝም ሀብቷ ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ አቅም እንዳላት ሚኒስትር ዴኤታዋ አመልክተዋል፡፡

የቱሪዝም ቀን መከበር ዐቢይ ዓላማው በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ ቱሪዝም ያለውን ጠቀሜታና የሚኖረውን ማኅበራዊና ባህላዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚክ እሴቶችን ማስገንዘብ ነው፡፡

በዓሉ የሚከበርበት ቀን የተመረጠው በሰሜናዊውም ሆነ ደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የወቅቶች መሸጋገሪያ በመሆኑ ነው፡፡ በሰሜኑ ክረምት የሚገባበት፣ በደቡቡ (ኢትዮጽያ ያለችበት) መፀው የሚብትበት አጋጣሚ ይውላል፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ ተቋም እምነት ሀገራት በየዓመቱ በልዩ አከባበር እንዲያከብሩት ፍላጎት አለው፡፡

በኢትዮጵያ በዓሉ ከብሔራዊው በዓል ደመራና መስቀል ጋር በመግጠሙ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ በዓሉ በየአራት ዓመቱ የደመራ ዕለት (መስከረም 16) ሦስቱን ዓመታት ግን በመስቀል ዕለት (መስከረም 17) ይከበራል፡፡ በ1973 ዓ.ም. በየሀገራቱ ይከበር የነበረው የዓለም የቱሪዝም ቀን ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ ከዓለም አቀፍ ድርጅቱ ጋር በመሆን በተለይ በአስተናጋጅ ሀገሮች እንዲከበርም ተደርጓል፡፡

በ1996 ዓ.ም. በተወሰነው ውሳኔም በዓሉን በየዓመቱ በዋናነት የሚያዘጋጁት ሀገሮች አኅጉራት በቅደም ተከተል በማስተናገድ ላይ ናቸው፡፡ በ1999 ዓ.ም. በአውሮፓ (ፖርቱጋል"፣ በ2000 ዓ.ም. በደቡብ እስያ (ስሪላንካ) በማዕከልነት ሲከበሩ የዘንድሮው ተረኛ የአሜሪካዋ ፔሩ ስትሆን ለ2002 ዓ.ም. ተረኛዋ አፍሪካ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ሦስተኛውን ሺሕ ዘመን በተቀበለችበት ማግሥት የከርሞውን በዓል በማዕከልነት ለማዘጋጀት ዕድሉን እንድታገኝ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ታሪካዊት ጅማ - የ2001 ዓ.ም. ቱሪዝም ቀን መዲና


የዘንድሮ የዓለም ቱሪዝም ቀን በብሔራዊ ደረጃ የተከበረባት ጂማ በነባር ታሪኳ የአምስቱ የጊቤ ራስ ገዝ መንግሥታት መካከል ከጠንካራዎቹ መካከል ትጠቀሳለች፡፡ እስከ ባሕር ዳርቻ የዘለቀ የንግድ መስመር የተዘረጋባት ሒርማታ የተሰኘ ጥንታዊ የሐሙስ ገበያ ማዕከል ያላት ናት፡፡ በውጮች ዘንድ "ኮፊ" የተሰኘው ቡና መገኛ ከፋ ሲሆን የገበያ መዳረሻው ጂማ ነው፡፡ ከጂማ ሰሜን አቅጣጫ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በጅሬን የሚገኘው የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ዐቢዩ መስሕብ ነው፡፡ ቤተ መንግሥቱ መስጊዱንና ልዩ ልዩ ሕንፃዎች አካትቷል፡፡

በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ጊዜ ጅማ "የኦሮሞና ሲዳማ" ክልል መዲና የነበረች ሲሆን ዘመናዊነቷን ለማሳየት "ፒኮሎ ሮማ" (ትንሿ ሮማ) ይሏትም ነበር፡፡

የጂማው አከባበር ቱሪዝም ተኮር ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ሲምፖዚየም፣ ከመሪ ሐሳቡ በመነሳትም በአባ ጂፋር ቤተ መንግሥት ግቢ የችግኝ ተከላም ይካሄዳል፡፡ በተመሳሳይ በዓሉ በጋምቤላ የሚከበር ሲሆን በሁሉም ስፍራ የቱሪስት መስህብ ቦታዎች እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡
 
< Prev   Next >