Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቅ አዲስ ሲዲ ተለቀቀ
ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቅ አዲስ ሲዲ ተለቀቀ E-mail
Sunday, 28 September 2008

Imageባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በቅርቡ ያሳተመውና ያሰራጨው ሲዲ "Discover the Real Ethiopia" ረእውነተኛዋን ኢትዮጵያ ይቃ"ትሪ የኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ መስህቦች ምንነትና ይዘት ያስተዋውቃል፡፡ የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ከታሪካዊ መረጃዎች በመጣጥፍ፣ በፎቶ ግራፍ፣ በሥዕልና በቪዲዮ ክሊኘስ ተቀናብሮ የቀረበ ነው፡፡

 

ይህ በ3ኛው ሺሕ ዓመት ዋዜማ የተለቀቀው ሲዲ ለቱሪስቶች፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ የጉዞ ወኪሎች ለመገናኛ ብዙኀን ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡

በሲዲው ውስጥ ያለው ብሩሸር 12 ርእሰ ጉዳዮችን ከሙዚቃዊ ዳራ ጋር አካትቶ ይዟል፡፡ በመግቢያው እንደተመለከተው ቱሪስቶችም ሆኑ ሌሎች ለመጎብኘት የሚፈልጉትን አካባቢ ቅዱሳት መካናት፣ ሃይማኖታዊ ተቋማት ጥናት፣ የባህልና ዕፅዋት ብሔራዊ ፓርኮችን፣ የተፈጥሮ ደኖችን ገጽታ መረጃ ይሰጣል፡፡

ሃይማኖታዊ ንግደት (Pilgrimage) በኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን ለማንገሥ በተለያዩ አካባቢዎች ጉዞ የሚደረግባቸውን ስፍራዎች ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዋናነት የሚታወቁት መካኖች በሲዲው ተዘርዝረዋል፡፡ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ ዳሞ፣ ላሊበላ፣ ግሸን ማርያም፣ የጣና ደሴቶች ገዳማት፣ ቁልቢ ገብርኤል፣ ደብረ ሊባኖስ፣ ዝቋላ አቦ፣ አዳዲ ማርያም ሲሆኑ፣ የሙስሊም ኅብረተሰቡ ዋና መካናት ነጃሽ መስጊድ፣ ሼክ ሁሴንና ሶፍ ዑመርም ተጠቅሰዋል፡፡

ከጥናትና ምርምር አኳያ ሁሉም ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የቱሪዝም መስህቦች ለተመራማሪ ምሁራን ለዕውቀት መስካቸው ተጨማሪ ዕውቀት የሚያገኙበት አጋጣሚ ይፈጥርላቸዋል፡፡ ትምህርታዊ ጉዞም ያደርጋሉ፡፡

በአፋር ኤርታሌ ያለማቋረጥ የሚታየው እሳተ ገሞራ አንዱ መስህብ ነው፡፡ 83 ብሔረሰቦች የሚኖሩባት አገር ልዩ ልዩ ባህላዊ ገጽታዎችና ልምምዶች የገዳ ባህላዊ ሥልጣንና የመሳሰሉት ከጥናት መስክ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

ሲዲው የኢትዮጵያ ሥርወ መንግሥታት አነሳስና ታሪክ፣ የአክሱም ንግሥና፣ የመካከለኛ ዘመኗን ጎንደር፣ ሐረር፣ ላሊበላ፣ ጅማ፣ የዛጉዌ አብያተ ክርስቲያናት ቅድመ አክሱም፣ ቅድመ ታሪክ-ሐዳር፣ ስለንግሥተ ሳባ፣ ስለ አዲስ አበባ መሠረታዊ ታሪኮች ተዘግቦበታል፡፡

ሲዲው ካካተታቸው ምስሎች መካከል የኢትዮጵያ ሕዝብን ልዩ ልዩ መልኮች፣ መልክዐ ምድር፣ የጢስ ዓባይ፣ የጣና፣ የሐዋሳ ሐይቅ፣ አዕዋፋት፣ የገበያ ስፍራዎች ታሪካዊ ቦታዎችና ክብረ በዓላት ይገኙበታል፡፡
Last Updated ( Sunday, 28 September 2008 )
 
< Prev   Next >