| የዓመቱ የሠላም ሽልማት ለዩኔስኮ ተበረከተ |
|
| Sunday, 28 September 2008 | |
|
ለሠላም መስፈን በተለያዩ እምነቶች መካከል ጥሩ የመቀራረብ መንፈስ በመፍጠር የሚንቀሳቀሰው ኢንተርፊይዝ ፒስ ቢዩልዲንግ ኢኒሽየቲቭ (አይ.ፒ.አይ) ለተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓመቱን የሠላም ሽልማት መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የዓለም የሠላም ቀን በአፍሪካ ሕብረት የስብሰባ አዳራሽ መስከረም 12 ቀን 2001 በተከበረበት ሥነስርዓት ላይ ተገኝተው ሽልማቱን የተቀበሉት በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተወካይ ሲሆኑ የዋንጫ፣ የሜዳሊያና የሰርቲፊኬት ሽልማቱን በየተራ የሰጡት ደግሞ የአይ.ፒ.አይ የቦርድ አባላት ናቸው፡፡ ተወካዩ ሽልማቱን ከተቀበሉ በኋላ ድርጅቱ የሚያካሂደውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው የሃይማኖት አባቶችም ለሠላም የበለጠ እንዲሠሩ አሳስበዋል፡፡ የዘንድሮው የሠላም ሽልማት ፕሮግራም በአይ.ፒ.አይ በኩል ሲካሄድ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን የመጀመሪያው ተሸላሚ በሠላምና ግጭት አፈታት የካበተ ልምድ ያላቸው ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ ናቸው፡፡ የሁለተኛው ተሸላሚ ደግሞ በ1997 አገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በመንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተፈጠረው ውዝግብ በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የአገር ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |