Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ዲኬቲ ከ650 ሚሊዮን በላይ ኮንዶሞችን አሰራጨ
ዲኬቲ ከ650 ሚሊዮን በላይ ኮንዶሞችን አሰራጨ E-mail
Sunday, 28 September 2008

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ከ1982 ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ አሥራ ሰባት ዓመታት ከ650 ሚሊዮን በላይ የወንድና የሴት ኮንዶሞችንና ከ23 ሚሊዮን የሚበልጡ በአፍ የሚወሰዱ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎችን በማሠራጨት ለማኅበራዊ ጤና ፕሮግራሞች ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስታወቀ፡፡

 

ከዚህም ሌላ ከ14 ሚሊዮን ብልቃጥ በላይ በመርፌ የሚሰጡ፣ ከ14 ሺህ በላይ በማህፀን የሚቀመጡ፣ ከ21 ሺህ 500 በላይ የሚቀበሩና ከ20 ሺህ በላይ ድንገተኛ የወሊድ መቆጣጠሪያዎች ማከፋፈሉን አስረድቷል፡፡

በወሊድ ጊዜ በእናቶች ላይ የሚደርሰውን የደም መፍሰስ ለመከላከል ወይም ለመቀነስ የሚረዱ 65 ሺህ የሚሰፕሮስቶል እንክብሎችን፣ ተቅማጥን ተከትሎ የሚከሰተውን የሰውነት ፈሳሽ ማለቅ ለማከም የሚያግዙ ከ7 ሚሊዮን በላይ የሰውነት ፈሳሽ መተኪያ ንጥረ ነገር ከረጢቶች ማከፋፈሉንም አስታውቋል፡፡

በዲኬቲ የማኅበራዊ ግብይት ዘዴ የተለያዩ ጤና ነክ ምርቶችን በተለይም ኮንዶሞችንና ሌሎች የወሊድ መከላከያዎችን ለማስተዋወቅ የግብይት መንገድን እንደሚጠቀም፣ ምርቶች በቀላሉ እንዲገኙም በአገሪቱ በሚገኙ የመድሀኒት ቤቶችና ሌሎች ፈቃድ ባላቸው የግል ድርጅቶችና በመሸጫ መደብሮች አማካይነት እንደሚያሠራጭ አመልክቷል፡፡

የአየርላንድ እርዳታ ድርጅት፣ የኔዘርላንድስ ኤምባሲና የእንግሊዝ የዓለም አቀፍ ልማት ድርጁት (ዲ ኤፍ አይ ዲ) ዲኬቲ ኢትዮጵያ በስነተዋልዶ ጤና፣ ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከል፣ በእናቶችና ህፃናት ጤና ዙሪያ ለሶስት ዓመታት የሚያከናውናቸውን የማህበራዊ ግብይት እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ የሚያስችል የ18.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ደላር እርዳታ እንደሚሰጡም ዲኬቲ ጠቁሟል፡፡
 
< Prev   Next >