Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ኢትዮጵያ ሙስናን በመዋጋት ረገድ...
ኢትዮጵያ ሙስናን በመዋጋት ረገድ... E-mail
Wednesday, 01 October 2008
ኢትዮጵያ ሙስናን በመዋጋት ረገድ መሻሻል ማሳየቷ ተመሰከረ

በጋዜጣው ሪፖርተር

መቀመጫውን በርሊን ያደረገው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በሙስና ረገድ ኢትዮጵያ አምና ከነበረችበት 138 ደረጃ ዘንድሮ ወደ 126ኛ መሻሻል ማሳየቷን አስታወቀ፡፡

በትራንስፓረንሲ ሪፖርት መሠረት በ126ኛ ደረጃ ከተቀመጡት ሌሎች አገራት ማለትም ኢንዶኔዥያ፣ ጉዋና፣ ሊቢያ፣ ኤርትራ እና ሞዛምቢክ ተርታ ኢትዮጵያም መግባቷን ድርጅቱ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የ2008 ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በይበልጥ በሙስና የተዘፈቁ አገራት በሚል ድርጅቱ የጠቀሳቸው ቻድ፣ ሱዳን፣ ጊኒ እና ሶማሊያን ነው፡፡

በአንፃሩ ዝቅተኛ የሙስና ሁኔታ ይታይባቸዋል በሚል ከጠቀሳቸው አገራት መካከል ዴንማርክ፣ ስዊድን፣ ሲንጋፖር፣ ፊንላንድ፣ ስዊዘርላንድ፣ አይስላንድ፣ ኔዘርላንድ፣ አውስትራሊያና ካናዳ ይገኙበታል፡፡
 
< Prev   Next >