Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በጂጂጋ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ...
በጂጂጋ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ... E-mail
Wednesday, 01 October 2008
በጂጂጋ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ አራት ሰዎች ሞቱ፣ ሰባት ቆሰሉ

በታምሩ ጽጌ

በሱማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጂጂጋ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ ከሰዓት በፊት በደረሰ የፍንዳታ አደጋ አራት ሰዎች ሞተው ሰባት ሰዎች ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው በስፍራው የተገኙ የዓይን እማኞች ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡

እሑድ መስከረም 18 ቀን 2001 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በከተማው ቀበሌ 03 በተለምዶ አጠራር አፍሪካ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው አንድነት ሆቴል በራፍ አካባቢ ፍንዳታው መድረሱን የዓይን እማኞቹ ገልፀዋል፡፡

አደጋ የደረሰው በሆቴሉ በራፍ ፊት ለፊት በሚገኝ አንድ ዛፍ ስር በጀሪካን ውስጥ ተደርጐ የተቀመጠ ፈንጅ መሆኑን የገለፁት እማኞቹ፣ ምናልባት በሰዓት የተሞላ ሳይሆን እንደማይቀር ጥርጥሬያቸውን ተናግረዋል፡፡

ፍንዳታው በደረሰበት ሰዓት በአካባቢው የተገኙ አንድ የባጃጅ ሹፌርና በአንድነት ሆቴል ውስጥ ይስተናገዱ የነበሩ ሦስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን እማኞቹ ተናግረዋል፡፡

በደረሰው ፍንዳታ የአንድነት ሆቴል በሮችና መስኮቶች መስታዎቶቻቸው መሰባበሩን፣ በአካባቢው ያሉ ቤቶችና ሱቆችም መስታዎቶቻቸው መሰነጣጠቃቸውንና ፈንጂው የተቀመጠበት አስፓልት ወደ ውስጥ ተሰርጉዶ መመልከታቸውን እማኞቹ ገልፀዋል፡፡

ከፍተኛና መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰባት ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን፣ ነገር ግን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ሙሉ መረጃ እንደሌላቸው እማኞቹ ተናግረዋል፡፡

በጂጂጋ ከተማ ከትናንት በስቲያ በደረሰው ፍንዳታ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን፣ የፈንጂውን ዓይነት ለማወቅ ባለሙያዎች ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን የተናገሩት የዓይን እማኞቹ በንፁሀን ዜጐች ላይ የደረሰው የሞትና የአካል ጉዳት እንዳሳዘናቸው ገልፀው፣ ህብረተሰቡ የሚጠራጠራቸውን ሰዎች ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ ህገወጥ ሥራዎችን በጋራ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
 
< Prev   Next >