| የጆርጅ ቡሽን እቅድ ኮንግረሱ... |
|
| Wednesday, 01 October 2008 | |
|
የጆርጅ ቡሽን እቅድ ኮንግረሱ ውድቅ አደረገው
- አሜሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታለች በጋዜጣው ሪፖርተር የአሜሪካ ኮንግረስ የአሜሪካ የፋይናንስ ተቋማትን ለመታደግ የቡሽ አስተዳደር ያቀረበውን የ700 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ዕቅድ ውድቅ አደረገ፡፡ ጆርጅ ቡሽ በኮንግረሱ ውሳኔ ማዘናቸው ሲገለጽ የኮንግረሱን ውሳኔ ተከትሎ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ በዓለም ላይ እየደረሰ ነው፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱን ለመታደግ የወጣው ዕቅድ ላይ ከፍተኛ ክርክር ኮንግረሱ ካካሄደ በኋላ 228 በ205 በሆነ ድምጽ የቀረበውን የ700 ቢሊዮን ዶላር ወይም 380 ቢሊዮን ፓውንድ የመታደጊያ እቅድ ውድቅ አድርጎታል፡፡ እቅዱን ሁለት ሶስተኛው የሚሆኑ ሪፐብሊካኖች እንዲሁም 95 ዴሞክራቶች ሳይደግፉ በመቅረታቸው የፋይናንስ ተቋማትን መንግሥት እንዲረዳ የቀረበው ሰነድ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡ የኮንግረሱን ውሳኔ ተከትሎ ከፍተኛ ቀውስ በአሜሪካና በሌሎች አገራት እየደረሰ ነው፡፡ ጆርጅ ቡሽ ስልጣናቸው ሊያበቃ በደረሰበት ወቅት በተከሰተው ቀውስ የተደናገጡ ሲሆን፣ ኮንግረሱ እቅዳቸውን ባለመጽደቁም ከፍተኛ ሀዘኔታ ላይ ወድቀዋል፡፡ አሜሪካም ወደከፋ የኢኮኖሚ ቀውስ እንደምትገባ ጆርጅ ቡሽ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ቢሆንም ኮንግረሱ ግን የአሜሪካ መንግሥት የፋይናንስ ተቋማቱን መደገፍ የለበትም በሚል ድምጽ ሰጥቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በቀጣይ ጉዳይ ላይ ለመወሰን ጆርጅ ቡሽ የኢኮኖሚ አማካሪዎቻቸውን ይሰባሰባሉ ተብሏል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ውሳኔን ተከትሎ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ቀውስ እየደረሰ ነው፡፡ በአሜሪካ በ4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዋቾቪያ ባንክ ሲቲ ግሩፕ ለተባለ ባንክ ተሽጧል፡፡ የቤንሉክስ ባንክ በኔዘርላንድ፣ በቤልጂየምና በሉክሰንበርግ መንግሥታት በከፊል ተገዝቷል፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ብራድ ፎርድና ቢንጊሊ የተባሉትን ባንኮች መግዛቱን ሲያስታውቅ በፈረንሳይ ያለው የባንክ አለምአቀፍ ሼር በአምስት በመቶ እንዲሁም የጀርመን በአራት በመቶ ወርዷል፡፡ ይህ የኢኮኖሚ ቀውስ ሁሉንም የአለም አገራት ወዳልተጠበቀ ቀውስ ይመራል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |