Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow መለስ የሶማሊያ ባህር አጋቾች...
መለስ የሶማሊያ ባህር አጋቾች... E-mail
Wednesday, 01 October 2008
መለስ የሶማሊያ ባህር አጋቾች ጉዳይ አሳስቧቸዋል
 
በጋዜጣው ሪፖርተር

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በቅርቡ የጦር መሳሪያ የጫነችው የዩክሬይን መርከብ በሶማሊያ አጋቾች ቁጥጥር ስር መዋሏ እንዳሳሰባቸውና አካባቢው ለማተራመስ ጥቅም ላይ እንዳይውል ስጋት እንዳደረባቸው የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ፡፡

አቶ መለስ በኒውዮርክ ከተማ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኮንደሌዛ ራይስ ጋር ባደረጉት ውይይት በሶማሊያ ባህር ጠረፍ አካባቢ ያለው እገታ "እጅግ አሳሳቢ ችግር" ላይ መድረሱና ለጉዳዩ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ ይሰጣል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ መለስ ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "በሶማሊያ ባህር ያለው የእገታ ደረጃ እጅግ አሳስቦናል፡፡ ከሶማሊያ ካለው አለመረጋጋትም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ነው" ብለዋል፡፡

ይህች ወደ ኬንያ ስትጓዝ የነበረችው የዩክሬይን መርከብ 33 ታንኮች፣ ከፍተኛ ላውንቸሮች፣ ጥይቶችና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች የጫነች ሲሆን፣ በቁጥጥር ስር የዋሏት የሶማሊያ አጋቾች 22 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠይቀዋል፡፡ አቶ መለስ ስጋታቸውን ሲገልፁ፣ "ይህንን ሁሉ የጦር መሳሪያ አካባቢው ለማተራመስ ጥቅም ላይ ሊያውሉት ይችላሉ፣ በመሆኑም በሶማሊያ ባህር አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለሁላችንም አሳሳቢ ነው" ብለዋል፡፡ የዓለም ማህበረሰብ ሁኔታው አሳሳቢነት ተረድቶ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥም ጠይቀዋል፡፡

የሶማሊያ አጋቾች በዚሁ የፈረንጆች ዓመት ብቻ ከ30 በላይ መርከቦችን በማገት፣ በአካባቢው ያለው ባህር በአለም ትልቁ አደገኛ ቀጣና እንዲሆን ማድረጋቸውን፣ በእስያና በአውሮፓ የሚደረገው የንግድ ግንኙነት ስጋት እንደጣለባት ይታወቃል፡፡ ዘራፊዎቹ ከፍተኛ ካሳ የሚጠይቁ ሲሆን፣ አንዳንድ ጊዜም ሳያገኙ አለቀሩም፡፡

በደቡብ ሶማሊያ የሚገኘው እስላማዊ ዓማጺ ቡድን፣ የሶማሊያ ሽግግር መንግሥት የባህር ቁጥጥር እንዳያደርግ እንቅፋት ሆኖታል፡፡ ሩሲያ ባለፈው ዓርብ ዜጎቿና መርከቦቿን ደህንነት ለመጠበቅ ወደ አካባቢው የውጊያ መርከብ እንደምትልክ ባለፈው ዓርብ ማሳወቋ ይታወሳል፡፡
Last Updated ( Wednesday, 01 October 2008 )
 
< Prev   Next >