Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Friday
Nov 21st
Home arrow Sections arrow ብሔራዊ ኢንሹራንስ የግንባታ...
ብሔራዊ ኢንሹራንስ የግንባታ... E-mail
Wednesday, 01 October 2008
ብሔራዊ ኢንሹራንስ የግንባታ ፈቃድ እንዳልተሰጠው ገለፀ

- ሁዳ ሪል እስቴት የግንባታ ውል በማሳለፉ የደረሰው የቃል ማስጠንቀቂያ ብቻ ነው

በኃይሌ ሙሉ

በአዲስ አበባ ቴዎድሮስ አደባባይ አጠገብ ባለዘጠኝ ፎቅ ህንፃ ለመስራት በ1988 ዓ.ም. መሬት በሊዝ የተረከበው ብሔራዊ ኢንሹራንስ (ናይስ ኢንሹራንስ) እስከ አሁን ድረስ የግንባታ ፈቃድ እንዳልተሰጠውና ሊወሰድበት እንደነበር ገለፀ፡፡ በ1991 ዓ.ም ፒያሳ ያለውን ቦታ የተረከበው ሁዳ ሪል ስቴት ግን የግንባታ ፈቃድ ወስዶ ሳይሰራ በመቅረቱ እስካሁን የተሰጠው የቃል ማስጠንቀቂያ ብቻ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ብሔራዊ ኢንሹራንስ ቴዎድሮስ አካባቢ በሚገኝ ቦታ ላይ ህንፃ ለመገንባት በ1988 ዓ.ም. ከሊዝ ቦርድ ጋር ተስማምቶ ቦታ ቢረከብም እስካሁን ድረስ የግንባታ ፈቃድ መከልከሉን ገል"ል፡፡

የብሔራዊ (ናይስ) ኢንሹራንስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሀብተማሪያም ሹም ግዛው እንደገለፁት ድርጅታቸው በ1988 ዓ.ም. በ2 ሚሊዮን ብር ወጪ ቴዎድሮስ አደባባይ ከሜጋ አምፊ ቴአትር ፊት ለፊት የሚገኘውን ቦታ በሊዝ ቢገዛም እስከ አሁን ድረስ የግንባታ ፈቃድ አልተሰጠውም፡፡

ድርጅታቸው በሊዝ በተረከበው ቦታ ላይ የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጠው ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱን የገለፁት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፣ የግንባታ ፈቃድ የሚሰጡት ክፍሎች ግን የተለያዩ ምክንያቶች እያቀረቡ እስካሁን ድረስ ተፈፃሚ እንዳላደረጉት አስረድተዋል፡፡ የግንባታ ፈቃድ ተከልክለው ሳሉ ግንባታ አልጀመራችሁም ብሎ በጨረታ ለመሸጥ ተፈልጎ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

"አራዳ ክፍለ ከተማ በተረከባችሁት ቦታ ላይ ግንባታ አልጀመራችሁም ብሎ ቦታውን በጨረታ ሊሸጠው ነበር፡፡ የግንባታ ፈቀድ ሳይሰጠን እንዴት ሥራ ልንጀምር እንችላለን" ይላሉ አቶ ሃብተማርያም፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ የሊዝ አፈፃፀም ቡድን መሪ፣ አቶ መንግሥተአብ፣ ብሔራዊ ኢንሹራንስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም በተረከበው ቦታ ላይ ግንባታ ባለመፈፀሙ ቦታው ለሌላ አልሚ በጨረታ ተሸጦ እንደነበር አስታውሰዋል፣ ኋላ ላይ ግን የአስተዳደሩ ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ዶ/ር ውብሸት ብርሃኑ ለክፍለ ከተሞች ባስተላለፉት መመሪያ በመዲናዋ በሚገኙ ክፍለ ከተሞች እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ችግር ስላለ ውሳኔ አስከሚሰጥባቸው ድረስ ሁሉም ባለበት እንዲቆይ ባስተላለፉት መመሪያ መሠረት መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የሊዝ አፈፃፀም ቡድን መሪው፣ እንደሚሉት በብሔራዊ ኢንሹራንስ የተወሰደው ቦታ ለሌሎች አልሚዎች በጨረታ ቢሸጥ ኖሮ የግንባታ ጊዜ ያለፈባቸው ሌሎች ቦታዎችም በተመሳሳይ መልኩ በጨረታ ይሸጡ ነበር፡፡ ክፍለ ከተማው በብሔራዊ ኢንሹራንስ የተጀመረውን በሁዳ ሪል እስቴትም ለመድገም እቅድ የነበረው ቢሆንም በቀድሞው አስተዳደሩ ሥራ አስኪያጅ መመሪያ መሠረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

በቀጣይ ግን አዲሱ አስተዳደር ተደራጅቶ ስራ ሲጀምር በጉዳዩ ላይ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር አቶ መንግሥተአብ አስታውቀዋል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ የሊዝ አፈፃፀም ቡድን መሪ፣ ብሔራዊ ኢንሹራንስ በተረከበው ቦታ ላይ ግንባታ ባለመፈፀሙ በጨረታ ሊሸጥ እንደነበር ቢናገሩም ብሔራዊ ኢንሹራንስ ግን በተቃራኒው እስከአሁን ድረስ የግንባታ ፈቃድ እንዳልተሰጠው ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጿል፡፡

አንዳንዶች የግንባታ ፈቃድ ሳይሰጡ ካልጀመራችሁ ተብለው ጨረታ ይወጣባችኋል ሲባሉ፣ "የማዘጋጃ ቤቱ አጠገብ ቦታ ግን ለምን ጨረታ አልወጣበትም?" የሚል ጥያቄ አቅርበንላቸው ነበር፡፡

ፒያሳ አራዳ ጊዮርጊስ ፊት ለፊት የሚገኘው ክፍት ቦታ በ1991 ዓ.ም. በማዕከል ደረጃ ከንቲባው በተገኙበት፣ በሊዝ ቦርድ ተወስኖ እና አስፈላጊው ክፍያ ተፈፅሞ ግንባታ የሚያከናውነው ድርጅት ቦታውን መረከቡን ያስታወሱት አቶ መንግሥተአብ፣ ሁዳ ሪል እስቴት ቦታውን ከተረከበ ረጅም ዓመታት የቆየ ቢሆንም ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩኘ በአገሪቱ ውስጥ የሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች በርካታ በመሆናቸው እና የፒያሳውን ሲቲ ሴንተርም ውሎ አድሮ መሠራቱ አይቀርም፤ በሚል እሳቤ ግፊት እንዳልተደረገበት ተናግረዋል፡፡ ሁዳ ሪል እስቴት ግንባታውን እንዲጀምር የሚያሳስብ ማስጠንቀቂያ የተሰጠውም በቃል ብቻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አራዳ ክፍለ ከተማ በ1998 ዓ.ም. ለሁዳ ሪል እስቴት የቃል ማስጠንቀቂያ ከሰጠው በኋላ ድርጅቱ የቁፋሮ ስራ ጀምሮ እንደነበርና በኋላ ግን ስራው መቋረጡን አቶ መንግሥተአብ ገልፀዋል፡፡

"አንድ ድርጅት በልማት ስራ ላይ የሚንቀሳቀስ ቢሆንም ለ1ዐ ዓመታት ያህል ሳይገነባ ሲቀር በዝምታ መመልከት ተጠያቂ አያደርግም ወይ?" ለሚለው አቶ መንግሥተአብ ሲመልሱ "አሥር ዓመት ረጅም ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ችግር ያለው በአራዳ ክፍለ ከተማ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ጭምር ነው" ብለዋል፡፡

አቶ መንግሥተአብ እንደሚሉት በሁዳ ሪል እስቴት ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ እንቅፋት የፈጠረው ሌላው ምክንያት የቀድሞው የአዲስ አበባ ባለአደራ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ያስተላለፉት መመሪያ ነው፡፡
 
< Prev   Next >