|
ቅጥ አንባሩ የጠፋው የእግር ኳስ ፌዴሬሽን |
|
|
Wednesday, 01 October 2008 |
|
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራር መካከል የተፈጠረ አለመግባባት ስር ሰዶ የእነ አቶ አብነት ቡድን፣ እነ ዶ/ር አሸብርን አሰናብቷል፡፡ እነ ዶክተር አሸብርም ለዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) አቤቱታ አቅርበው ፊፋ ጉዳዩን ለመፍታት ያዘጋጀው የመፍትሄ ሃሳብ (ሮድ ማፕ) ልኳል፡፡
ከፊፋ ዕውቅና የተነፈገው አዲሱ አመራር ሮድማፑን መተግበር ባለመቻሉ አገሪቱ ለቅጣት ተዳርጋለች፡፡ ይህም ሆኖ ንትርኩ ከመቀጠሉና መንግሥትም በስፖርት ጣልቃ አልገባም በሚል ስሜት ተመልካች ሆኖ ቀርቷል፡፡ ለነገሩ ፊፋ ጠቅላላ ጉባኤ ይካሄድና ተአማኒነት ባለው ምርጫ ጉዳዩ ይቋጭ የሚል አቋም አለው፡፡ የአዲሱ ፌዴሬሽን አመራር ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ማድረግ፣ አለበለዚያ ለቀድሞ አመራር ስልጣኑን ማስረከብ ለምን እንዳዳገተው ሊገባኝ አልቻለም፡ አሁንም መንግስት በጉዳዩ ጣልቃ በመግባት ውዝግቡ አገር በማይጎዳ መልኩ እንዲፈታ የበኩሉን በጎ እገዛ ያድርግ፡፡ ሁለቱም ወገኖች ከተራ የፌዴሬሽን ሥልጣን ሽኩቻ ይልቅ የአገር ጉዳይ ቀዳሚ መሆኑን ይገንዘቡና ሥልጣን የመልቀቅ መራራ መስዋዕትነትንም ቢሆን ለመክፈል ይዘጋጁ እላለሁ፡፡
(ምንተስኖት፣ ከአዲስ አበባ) |