| ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ... |
|
| Wednesday, 01 October 2008 | |
|
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሉሙምባሺ አዲስ በረራ ይጀምራል
በጋዜጣው ሪፖርተር ከመጪው ጥቅምት 17 ቀን ጀምሮ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተማ ሉሙምባሺ አዲስ በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሪፖርተር ጋዜጣ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በሳምንት ለአራት ቀናት በሉሙምባሺ የሚካሄደው የአውሮፕላን በረራ ከተማዋን ከዋና ዋና የእስያ፣ የአሜሪካንና የአውሮፓ ከተሞች ጋር እንድትገናኝ ያደርጋታል፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ግዛት ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችው ሉሙምባሺ የንግድ የፋብሪካ እንቅስቃሴ በስፋት የሚታይባት ስትሆን በጨርቃ ጨርቅ፣ በምግብ፣ በመጠጥና በመዳብ ምርቶችዋ ትታወቃለች፡፡ አየር መንገዱ 118 መቀመጫዎች ያሏቸው ቦይንግ 737 - 700 አውሮፕላኖችን እንደሚያሰማራ የተላከው መግለጫ ያመለክታል፡፡ በረራ የሚካሄድባቸው ቀኖች ሰኞ፣ ረቡዕ፣ አርብና ቅዳሜ ሲሆኑ መንገደኞች ለደርሶ መልስ ጉዞ 1"742 ብር እንደሚከፍሉ ተገልጿል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |