| የመንገድ ፅዳት ሠራተኞች ለአገልግሎት... |
|
| Monday, 21 January 2008 | |
|
የመንገድ ፅዳት ሠራተኞች ለአገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶች እንደሌላቸው ተጠቆመ የመንገድ ፅዳት ሠራተኞች በሕዝብ ትራንስፖርት (ታክሲና አወቶቡስ) ውስጥ ልብሳቸውን እንደሚቀይሩና ምሳቸውን የሚይዙበት ሳህንም ቆሻሻ በሚያጓጉዙበት ጋሪ ላይ እንደሚያስቀምጡ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ የዓለም ሥራ ድርጅት የምሥራቃዊ አፍሪካ ክፍለ አህጉራዊ ፅህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ያካሄደው ይኸው ጥናት እንዳመለከተው፣ የመንገድ ፅዳት ሠራተኞች ልብሳቸውን በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ ለመቀየር የተገደዱት ለዚህና ለሌላም አገልግሎት የሚውሉ መሠረታዊ አቅርቦቶች ስለሌላቸው ነው፡፡ ምግብ የያዘው ሳህን በቆሻሻ ማጓጓዣ ላይ ማስቀመጣቸው ለትንኮሳ፣ ለዛቻና ዝቅ ብለወ እንዲታዩ ደዳረጋቸው ጥናቱ አመልክቶ የእጅና የገላ መታጠቢያ አቅርቦት አለመኖርና በሥራ ላይ እያሉ የመመገብ ልማድ በግል ንፅህና አጠባበቃቸው ላይ የጎላ ተፅእኖ ማሳደሩን አስረድቷል፡፡ ከመንገድ ፅዳት ሠራተኞች መካከል 34 በመቶ ያህሉ ትኩሳትና ጉንፋን፣ 32 ከመቶ የሚሆኑት የዓይን ማሳከክ፣ 18.7 በመቶ ተቅማጥና የሆድ መታወክ፣ 16 በመቶው የአይን በሽታ አድሮባቸው እንደነበር ጥናቱ ጠቁሞ በአብዛኛው ለተለያዩ ከፍተኛ በሽታዎች የተጋለጡት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሠራተኞች መሆናቸውን ይህም ሊሆን የቻለው ከገበያው መተፋፈግ፣ እንዲሁም በአካባቢው ምቾት የሌላቸውና የተጨናነቁ መኖሪያ ቤቶች በብዛት ስላሉበት መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ከዚህም ሌላ 38.7 በመቶ የሚሆኑት የመቆረጥ፣ 13.3 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የጡንቻ መኮማተር፣ የትራፊክ አደጋ እና በአንዳንድ አምባጓሮ ፈጣሪዎች አማካይነት ጥቃት የደረሰባቸው መሆናቸውን ጥናቱ አስታወቋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |