| የመን ለመግባት ከሞከሩ ሶማሊያዊያን 52 ያህሉ ሞቱ < |
|
| Wednesday, 01 October 2008 | |
|
የኤዳንን ባህረ ሰላጤ በማቋረጥ በሕገወጥ መንገድ በማቋረጥ ወደየመን በጀልባ ለመግባት ሙከራ ያደረጉ ሶማሌያውያን መካከል 52 ያህሉ መሞታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የተመድ ዜና አገልግሎት ትላንት እንደዘገበው ሶማሊያዊያኑ ሊሞቱ የቻሉት የተሳፈሩበት ጀልባ በብልሽት ምክንያት ምግብና ውሃ በማያገኙበት ሁኔታ ከ18 ቀናት በላይ በመቆሙ ነው፡፡ ከ124 ያላነሱ ሰዎችን አሳፍሮ ነበር የተባለለት ይኸው ጀልባ 48 ሶማሊያዊያን በሕይወት መገኘታቸውን፣ ዕድሜያቸው ከ2 እስከ 40 እንደሚገመት ጠቅሷል፡፡ እስካሁን 52 ያህሉ መሞታቸው ሲረጋገጥ የተቀሩት የት እንደደረሱ አልታወቀም፡፡ ተሳፋሪዎቹ ለሕገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ወደ የመን ለመሻገር በነፍስ ወከፍ ከ70 እስከ 100 ዶላር ከፍለዋል፡፡ ኮሚሽኑ በያዝነው ዓመት ብቻ በሕገወጥ መንገድ 31ሺ 192 ሰዎች ወደየመን መግባታቸውን፣ 228 ሰዎች በጉዞ ላይ መሞታቸውን፣ 262 የደረሱበት አለመታወቁን ጨምሮ ገል..ል፡፡ የግብፅ ቱሪስት አጋቾች ተገደሉ ሱዳን ቱሪስቶችን ለማገት ሲንቀሳቀሱ ደርሼባቸዋለሁ ያለቻቸውን ስድስት አጋቾች መግደሏን አስታወቀች፡፡ 11 ቱሪስቶች እና 8 የግብፅ የቱሪስት አስጎብኚዎች የተገደሉት በሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ ነው፡፡ በመኪና ላይ ስምንት ታጣቂዎች ነበሩ፡፡ መኪናቸውን እንዲያቆሙ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ስድስቱ ታጣቂዎች ወዲያውኑ ተገድለዋል፡፡ ከሟቾቹ መካከልም የአጋቾቹ መሪ ነው የተባለ የቻድ ስም ያለው ግለሰብ ይገኝበታል፡፡ ተሽከርካሪው የግብፅ የሰሌዳ ቁጥር የነበረው እና በግብፅ የቱሪዝም ኩባንያ የተመዘገበ ነው፡፡ ለወባ 1.1 ቢሊየን ዶላር ተበረከተ የዓለም ባንክ አፍሪካ ወባን ለማጥፋት ለምታደርገው ርብርብ 1.1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሰጥ ቃል ገባ፡፡ ዕርዳታው በቀጣይ ሦስት ዓመታት ከወባ መከላከል ጋር በተያያዘ በአፍሪካ ለሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ይውላል፡፡ ወባ አምራች ኃይልን በማጥቃት አገራቱ የምዕተ ዓመቱን ግቦች ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት እየጎዳ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ዛምቢያ ወባን ለመከላከል አጎበሮችን በማደል፣ መድኃኒቶችን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ፣ የበሽታው መነሻ ለማጥፋት ያደረጉት ጥረት ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡ በሶማሊያ 15ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቀሉ በሶማሊያ አዲስ ከተቀሰቀሰው ውጊያ ጋር በተያያዘ 15ሺህ ያህል ሶማሌያውያን አካባቢያቸውን ለቀው መሰደዳቸው ተሰማ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የዜና ማዕከል የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው በሰሞኑ ውጊያ 80 ሰዎች መሞታቸውን በመቶ የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ታውቋል፡፡ አስከፊ ነው በተባለለትና በመንግሥት እና በእስልምና ም/ቤቶች መካከል በተቀሰቀሰው አዲስ ውጊያ እስከ 15ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን አዲሶቹን ስደተኞች ከጦርነቱ አካባቢዎች ማውጣትና ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ማጓጓዝ ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል፡፡ በምዕራብ ሶማሊያ የሚገኘው አፍጎዶ ጣቢያ ከ350ሺህ በላይ ስደተኞች መጨናነቁ የዕርዳታ ሰራተኞችን ክፉኛ አሳስቧል፡፡ በሰሜን ምዕራብ የሶማሊያ አጎራባች የሆነችው ኬንያ በየወሩ 5ሺህ ያህል ስደተኞች እንደሚሄዱ ዳባብ የተባለው ይኸው ካምፕ በአሁኑ ወቅት 215 ሺህ ያህል ስደተኞችን መያዙን አስታውቀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |