Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ኑሮን ለማሸነፍ...
ኑሮን ለማሸነፍ... E-mail
Wednesday, 01 October 2008
Imageበታደሰ ገብረማርያም

ለተ ብርሃን አብርሃ የ45 ዓመት ወይዘሪት ነች፡፡ ትዳርም ልጅም የሌላት ብቸኛ ነች፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ ያልሞከረችው የሥራ አይነት የለም፡፡ ቤይሩትም በተለያዩ ሰዎች ቤት ሰርታለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን አምባሻ እና ሻይ በመሸጥ ትተዳደራለች፡፡ ያገኘኋትም ቦሌ ትልቁ ድልድይ ውስጥ ቁጭ ብላ ይህንኑ ስትቸርችር ነው፡፡

"ኑሮ እንዴት ነው?" ብዬ ጠይኳት

"ለመኖር ያህል እንገዳገዳለሁ ይሄው እንደምታየው ይህንን እየቸረቸርኩ እኖራለሁ" በቀን ውስጥ ሶስት አምባሻና ግማሽ ኪሎ ሻይ ነው እመሸጠው፡፡ ከዚህ የዘለለም አልሄድኩም፡፡ አንድ አምባሻ አንድ ብር ከ75 ሳንቲም እሸጣለሁ፡፡ ትርፉ 25 ሳንቲም ብቻ ነው" አለችኝ፡፡ በአይኖቿ ላይ ያቀረሩትን እንባዎቿን በአንገት ልብሷ ጫፍ እየጠራረገች፡፡

በዚህ መልኩ እየቸረቸረች የምታገኛትን ገንዘብ በሙሉ ለቤት ኪራይ እንደምታውለው ለተብርሃን ገልጻ የቤት ኪራዩም 200 ብር መሆኑንና አሁንም አከራዮቹ የኪራይ ዋጋ እንጨምራለን መክፈል ከቻልሽ ትኖሪያለሽ ካልቻልሽ ደግሞ ጨርቅሽን ጠቅልለሽ በመውጣት ቤቱን ታስረከቢያለሽ እያሉ ጧትና ማታ እንደሚጨቀጭቋት አስረድታለች፡፡

ከምግብ ጋር ከተለያየች ሰንበትበት ማለቷን፣ የአምባሻ ዱቄት ስታቦካ፣ ስትጋግር፣ ስትቆርስና ስትሸጥ በአፍና በአፍንጫዋ የሚያውዳትን ሽታ የተመገበችው ያህል ስለሚሰማት ሆዷን በዚሁ እያታለለችው መሆኑን ትናግራለች፡፡ ከዚህ ውጭ አልፎ አልፎ ከሽያጭ የተረፈውን ከመመገብ በስተቀር ገንዘብ አውጥታ ለራሷ የሚሆን ምግብ የማዘጋጀት አቅም እንደሌላት ገልፃለች፡፡

"ትርፍ ከሌለው ይህንን ሥራ ለምን መረጥሽ፣ ሰው ቤት ለምን አትቀጠሪም?"

"ሰው ቤት መስራቱ ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ጭቅጭቁ ያስመርራል፡፡ በዛ ላይ ደግሞ እኔ ጉልበት የለኝም፡፡ ጤነኛ አይደለሁም፡፡ ዕድሜዬም እየገፋ ስለሄደ ሰው ቤት የመስራቱን ሃሳብ እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ፡፡ ያለኝ አማራጭ አሁን በያዝኩት ሥራ ራሴን ማስተዳደር ብቻ ነው፡፡ ካሁን በፊት ኢሕአዴግ ታጋዮች ዘንድ ተቀጥሬ ነበር፡፡ ምግባቸውን አዘጋጃለሁ፡፡ ቤቱን አጸዳለሁ፡፡ ሁኔታዎች ሁሉ ከአቅሜ በላይ ስለሆኑብኝ ለቅቄ ወጣሁ፡፡

አሁን የያዝኩት ሥራ ደግሞ ገበያ የለውም፡፡ ገበያ ያጣውም ሰው ሁሉ አምባሻ     በየቤቱ ስለሚሰራ ይህ አይነቱን ንግድ የሚያካሂዱ ሴቶች ቁጥር በጣም ስለበዙ ይመስለኛል፡፡ አልሆነልኝም እንጂ ቤይሩት ድረስ ሄጃለሁ፡፡

"ቤሩት ስንት ዓመት ኖርሽ"
"ሁለት ዓመት"
"ለምን ተመለሽ?
"ምግቡ ስላልተስማማኝና ስላመመኝ ነው የመጣሁት"
"የወር ደመወዝሽ ስንት ነበር?"
"በየወሩ 120 ዶላር ይከፈለኝ ነበር፡፡ ሥራ ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ ለሦስት ወራት ያህል አለምንም ደመወዝ በነፃ ነው ያገለገልኩት፡፡"

"ለምን?"

"ቋንቋ እስከምችል ድረስ ነው፡፡ ይህም ከመቀጠሬ በፊት ስለተነገረኝ አምኘበትና ተቀብዬው ነው ልገባ የቻልኩት"

"ሁለት አመት ስትቀመጭ አንድ ቤት ብቻ ነው የሰራሽው?"

 "እኔ ብዙ ቤት ነው የተንከራተትኩት፡፡ አንዲት ሰራተኛ ምንም ባይስማማት መጀመሪያ በተቀጠረችበት የሦስት ወር የግዴታ ጊዜዋን ካልጨረሰች ሌላ ቦታ ተቀይራ የመሥራት መብት የላትም፡፡ እኔም ብዙ ቤት ተዘዋውሬ ልሰራ የቻልኩት የግዴታ ጊዜዬን ስላጠናቀቅኩ ነው፡፡ የምሰራውም የፅዳት ሥራ ብቻ ነው፡፡

ተዘዋውራ በሰራችባቸው ቤቶች ብዙም የከፋ ነገር ባያጋጥማትም በምግብ ላይ አልፎ አልፎ ችግር ይፈጠርባት እንደነበር አስታውሳ፣ በተለይ በአንድ ወቀት በተቀጠረችበት ቤት ውስጥ አሰሪዋ ምግብ አውጥታ ካልሰጠቻት በስተቀር እራሷ አውጥታ መመገብ እንደማትችል አስረድታለች፡፡ "አንድ ጊዜ እርቦኝ ከስሀን ላይ አንስቸ ስበላ አሰሪዬ ደረሰችብኝ፡፡ ደነገጥኩና ወዲያውኑ በኪሴ ውስጥ አስቀመጥኩት፡፡ ከዛም እኔ ሳልሰጥሽ አንቺ ለምን አንሳሽ ብላ ተቆጣችኝ፡፡ ከዛ በኋላ እሷ ካልሰጠችኝ በስተቀር እኔ በገዛ እጄ አንስቼ በልቼ አላውቅም" በማለት በትካዜ መንፈስ ከፊት ለፊት ከተደቀኑት ፔርሙዞች መካከል አንደኛውን እያሻሸች ነገረችኝ፡፡

"ከሊባኖስ ይዘሽ በመጣሽው ገንዘብ ኑሮሽን ለማሻሻል አልሞከርሽም?"

"አይ" ችግረኛ ዘመዶች በብዛት ስለነበሩኝ ለእነሱ አከፋፍዬ ይሄው ዛሬ ባዶ እጄን አጨበጭባለሁ"

"ለምን አታገቢም?"

"ለኔ የሚስማማኝ ወይም የሚሆነኝ ሰው ስላላገኘሁ ነው፡፡ የሚስማማኝ ካገኘሁማ ጥሩ ነው፡፡ 
 
< Prev   Next >