| ኤጀንሲው ከ365 ሚሊዮን ብር... |
|
| Thursday, 02 October 2008 | |
|
ኤጀንሲው ከ365 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገቢዎች ኤጀንሲ በሐምሌ ወር 2000 ዓ.ም ከ365 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ ከተሰበሰበው ገቢ ውስጥ 110 ሚሊዮን ብር ያህሉ ታክስ ነክ ካልሆኑ፣ ከካፒታልና ከማዘጋጃ ቤት ገቢዎች የተገኘ መሆኑን፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ከ54 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው፣ ከታክስ ነክ ገቢዎች 253ሺ ነጥብ 8 ሚሊዮን ለመሰብሰው ታቅዶ ከ255 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) ባለሥልጣኑ አዲስ መመሪያ አዘጋጀ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ፕሮጀክቶች በሚካሄድበት ወቅት የአካባቢ ጥበቃንና የማኅበራዊ ልማትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለማከናወን የሚያስችለውን መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፕሮግራም፣ የመንገድ ደረጃና የአካባቢ ጥበቃ፣ ሰዎችን መልሶ ማቋቋምና የመንገድ ደህንነት መመሪያ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ (ዋኢማ) ለሴት ነጋዴዎች ድጋፍ ሊደረግ ነው ለኢትዮጵያ ሴት ላኪ ነጋዴዎች የሚደረጉ ድጋፎች ሴቶች በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር እንደሚያስችሉ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር ገልፀው፣ የስፔን መንግሥት ሴቶችን በዘርፉ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ድጋፍ እንደምታደርግ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሴት ላኪ ነጋዴዎች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የስፔን መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ፣ ተቀማጭነቱ አየር ላንድ ካደረገውና ኮኔክት ኢትዮጵያ ከተባለው የንግድ ማኅበረሰብ ጥምረት ጋር በመተባበር ከሌሎች በዓለም ላይ ተደማጭነት ካላቸው ሴት ነጋዴዎች ጋር የማገናኘቱ ሥራ መስራቱን ሴንተር ፎር አፍሪካን ውሜን ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት ገልጿል፡፡ (ዋኢማ) ኢትዮጵያዊው የዩኔስኮ ሎሬት ተሸላሚ ሆኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ፕሮፌሰር ጥሩ ሰው ተፈራ በትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የዩኔስኮ ሎሬት ተሸላሚ በመሆን ተመረጡ፡፡ ፕሮፌሰሩ ለዩኔስኮ ሽልማት ሊበቁ የቻሉት በትምህርትና ምርምር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካበረከቱ የዓለም ምሁራን ጋር ተወዳድረው አሸናፊ በመሆናቸው ነው፡፡ (ዋኢማ) ኮሚሽኑ የመንግስትን ገንዘብ መዝብረዋል ባላቸው ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መሰረተ የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በቡድን በመደራጀት ከ3ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስትን ገንዘብ መዝብረዋል ባላቸው አራት ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ መመስረቱን አስታወቀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራዳ ጊዮርጊስ ቅርንጫፍ የኮምፒዩተር ሠራተኛ የሆነው ግለሰብ ከባንኩ ደንበኞች ሂሳብ ላይ በመቀነስ ወደራሳቸው አካውንት በማዞርና በመጠቀም የመንግስት ገንዘብ መዝብረዋል ብሏል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |