| "ሳይንስ ዊዝ አፍሪካ" ኮንፈረንስ... |
|
| Monday, 21 January 2008 | |
|
"ሳይንስ ዊዝ አፍሪካ" ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ ታስተናግዳለች በአፍሪካ ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚናን ለማስፋፋትና ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለአምስት ቀናት የሚመክር ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ እንደምታስተናግድ አፍሮ ኒውስ የተባለ የዜና አውታር አስታወቀ፡፡ ከየካቲት 24 እስከ የካቲት 28 ቀን 2ዐዐዐ ድረስ "ሳይንስ ዊዝ አፍሪካ" በሚል ርዕስ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ይኸው ኮንፈረንስ በአህጉሪቱ በመካሄድ ላይ ያለውን ልማት ለማፋጠን ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚጫወቱት ሚና ከፍ የሚልበትን መንገድ እንደሚተልም የዜና አወታሩ አመልክቷል፡፡ ኮንፈረንሱን በመተባበር ያዘጋጁት የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽንና ኢንተሊጀንስ ኢን ሳይንስ መሆናቸውን የዜና አውታሩ አመልክቶ ይህም ሂደት የስትራቴጂ ምርምሮችን ለማሳደግ በአፍሪካና በአጋሮቿ መካከል ያለውን ጤናማ ግንኙነት እንደሚያሳይ አስረድቷል፡፡ ኮንፈረንሱ "ሳይንስ ኤንድ ኢኖቬሽን ፖሊሲ" የሚል መሪ-ሃሳብ ማንገቡን እንዲሁም የአፍሪካና የሌሎችም አህጉራት ከፍተኛ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የታወቁ ሳይንቲስቶች፣ የምርምር ኘሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ወዘተ. በኮንፈረንሱ ንግግር የሚያደርጉ መሆኑ ታውቋል፡፡ አፍሮ-ኒውስ ሚስተር አብዱሌ ጃኒ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሃፊን ጠቅሶ እንደዘገበው፣ በአፍሪካ ልማትን በማፋጠንና የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት የአፍሪካ አገሮች መዋዕለ ንዋያቸውን በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ ማፍሰስ ይኖርባቸዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |