Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በሃዋሳ የታጠረው መሬት ለእንስሳት...
በሃዋሳ የታጠረው መሬት ለእንስሳት... E-mail
Sunday, 05 October 2008
በሃዋሳ የታጠረው መሬት ለእንስሳት መጠበቂያ የተከለለ ነው

በጋዜጣው ሪፖርተር

በሃዋሳ ከተማ መዳረሻ የሚገኘው 3200 ሄክታር መሬት ለእንስሳት መጠበቂያ ተብሎ የተከለለ ሥፍራ (ኳራንቲን) መሆኑን የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎች የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ገለፀ፡፡
የሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ ይህን ያስታወቀው በሪፖርተር ጋዜጣ “የክቡር ሚኒስትር”ና በ”ተስፍሽና ገብርሽ” ገጽ ላይ በቀልድ ወይም በአሽሙር ተፃፈ ለሚላቸው አስተያየቶች በሰጠው መልስ ነው፡፡

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ከሚጠቀምባቸው ቦታዎች አንደኛ የሆነው ቦታ ወደተከለለው ቦታ የሚገቡትን እንስሳት ጤናቸውን ተንከባክቦ ደረጃውን የጠበቀ የከብት ሥራ ወደ ወጭ ለመላክ ይቻል ዘንድ ኩባንያው የሚጠቀምበትና ልዩና አስፈላጊ ኳራንቲን መሆኑን ገልፆ ታጥሮ የተቀመጠ ቦታ ነው የሚል ግምት መስጠቱን ተችቷል፡፡

ሥጋን ወደ ውጭ ለመላክ በተጣለው ማዕቀብ ምክንያት ለመጠቀም ባለመቻሉ ከመሬቱ አንድ ሶስተኛውን ለእርሻ ምርት ማዋሉን የሕዝብ ግንኙነቱ ይገልፃል፡፡ ሙሉ ቃሉን በእኔ የምለው ገጽ ይመልከቱ፡፡
 
< Prev   Next >