Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የአሜሪካው ኩባንያ ከአዲስ አበባ...
የአሜሪካው ኩባንያ ከአዲስ አበባ... E-mail
Sunday, 05 October 2008
የአሜሪካው ኩባንያ ከአዲስ አበባ የባቡር ሀዲድ ሥራ ውድድር ውጪ ሆነ

በአሰግድ ተፈራ

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ በሚዘረጋው የባቡር መስመር ሥራ ላወጣው ጨረታ ከተወዳደሩት ሶስት ድርጅቶች መካከል የአሜሪካኑ ኩባንያ በቴክኒክ ግምገማ ወደቀ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ጨረታ ከአሜሪካ፣ ከቻይናና ከጣሊያን ሶስት ኩባንያዎች ተወዳድረው ነበር፡፡ የጨረታ ኮሚቴው ባደረገው የቴክኒክ ግምገማ የአሜሪካኑ ኩባንያ ውድቅ ሆኗል፡፡ ለቦርዱ ቅርበት ያላቸው እንደጠቆሙት በትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ለሚመራው ቦርድ የቴክኒክ ግምገማው ሪፖርት ቀርቦ ሥራው ከሁለቱ ኩባንያዎች መካከል የተሻለ ገንዘብ ላቀረበው የሚሰጥበት ቀጣይ አካሄድ ይወሰናል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ፕላን ክፍል ጉዳዩን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄ በሂደት ላይ ያለ ጉዳይ በመሆኑ ዝርዝር ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡ የአሜሪካኑ ኩባንያ ከውድድሩ ስለመውጣቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገል..ል፡፡

በሌላ ዜና በመላ አገሪቱ ለሚገነባው የ5 ሺህ ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር ዝርጋታ ዲዛይን ለመሥራት አንድ የእንግሊዝ ኩባንያ ያለጨረታ መጋበዙ በኮርፖሬሽኑ ውስጥ ልዩነት ፈጥሯል፡፡

ልዩነት መፈጠሩን የጠቆሙት የኮርፖሬሽኑ ምንጮች ከአየር ላይ ዲዛይን ማሰራቱ በሥራ ሂደት ቀዳሚ አለመሆኑን ገልጸው በቅድሚያ ሊሰሩ የሚገባቸው ሥራዎች እንዳሉና ይሰራም ከተባለ በመንግሥት የጨረታ አሰራር መሠረት ሊኬድበት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
 
< Prev   Next >