Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ዳሽን ቢራ በሥራው ለመቆየት የቢራ...
ዳሽን ቢራ በሥራው ለመቆየት የቢራ... E-mail
Sunday, 05 October 2008
ዳሽን ቢራ በሥራው ለመቆየት የቢራ መደቦችን ለማጠፍ ዝግጅት እንዲደረግ አሳሰበ

በጋዜጣው ሪፖርተር

የዳሽን ቢራ፣ የደንበኞች የምርት አጠቃቀም፣ አቅም እየቀነሰ መሄዱን፣ በቢራ ኢንዱስትሪው ላይ የታየው የፍጆታ መዳከምና መቀዝቀዝ ማረጋገጫ እንደሆነና በሥራው ለመቆየት የቢራ መደቦችን ለማጠፍ ዝግጅት እንዲደረግ ዋና ሥራ አስኪያጁ አሳሰቡ፡፡
የዳሽን ቢራ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ አድማሱ ይህንን ያስታወቁት ..በሥራው ለመቆየት ሲባልና ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት.. የፋብሪካውን ወጪ መቀነስ አስመልክተው ለመምሪያ ኃላፊዎች በፃፉት ደብዳቤ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ..አለምአቀፋዊ ሁኔታ የፈጠረውን አሉታዊ ተጽዕኖ በጊዜያዊነትም ሆነ በቋሚነት የሚቋቋም የኢኮኖሚ አቅም አሁን.. እንደሌለ  የሚገልፁት የዳሽን ቢራ ሥራ አስኪያጅ፣ በደብዳቤያቸው ላይ በአገራችን የታየው የኑሮ ውድነት ምክንያት የዳሽን ቢራ ህልውና የማረጋገጥ ስትራቴጂ መከተል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

አሁን ያለው የገበያ ውድነት ሁኔታ ላሉት የቢራ አምራች ድርጅቶች በሙሉ አንድ አይነት ቢሆንም ..ይህ ችግር ዳሽን ቢራ ካሉት ከሌሎች የፋይናንስ ዕዳ/ብድር ሁኔታ ሲታይ የተለየ.. እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

ነገር ግን በደብዳቤያቸው ላይ ዳሽን ቢራ ከሌሎች የተለየ ነው ያሉበትን ብድር (ዕዳው) ስንት እንደሆነ አላመለከቱም፡፡

የገበያ ሁኔታው በዚህ ከቀጠለና ከፋብሪካው የገበያ ሥራ አፈፃፀም አቅም ጋር ያልተገናኘ መሆኑ ከተረጋገጠ፣ ከአሁኑ የወጭ ቅነሳ አሰራሮችን ማሰብ እንደሚገባ አቶ ብርሃኑ አመልክተዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ እንደሚሉት ..ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠትና በሥራው ለመቆየት አዲስ አሰራር መከተል ያስፈልጋል፡፡..

ስለዚህም መታጠፍ ያለባቸው የቢራ መደቦችን ለማጠፍ እስከሚደርስ ድረስ ዝግጅት ተደርጎ በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

በጀት የመከለስ፣ ከበጀት ውጭ ያለመሄድ፣ ለዝግጅት ተብለው የሚሰሩ ስራዎችን በመከለስ የወጭ ቅነሳ እንዲያደርግ ሥራ አስኪያጁ አሳስበዋል፡፡

እነዚህን ርምጃዎች የመውሰድ አስፈላጊነቱ ችግሮች ከፋብሪካው ቁጥጥር ውጪ ቢሆኑ ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ መሆኑን በደብዳቤው ላይ ተመልክቷል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ለመኖሪያዎችና ለአገልግሎቶች የፃፉትን ማስታወሻ ለዳሽን ቢራ ፋብሪካ ቦርድና ለጥረት በግልባጭ አስታውቀዋል፡፡  

በሌላ በኩል ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሠራተኞች የዋና ሥራ አስኪያጁን ማሳሰቢያ፣ መደብ በማጠፍ ስም ሠራተኞችን ለማባረር የተዘጋጀ አለማ ነው፤ ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

የዳሽን ቢራንና የሮያል የገበያ መቀዝቀዝ በኑሮ ውድነት መሳበቡን ሠራተኞቹ አይቀበሉትም፡፡ የሠራተኞችና የአስተዳደሩ ውጥረትና እንደ አንደኛው ምክንያት የሚያቀርቡት እነዚህ ሠራተኞች፣ አሁንም ቦርዱ መፍትሄ እንዲያፈላልግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ቀደም ሲል ከዳሽን ቢራ ሠራተኞች መባረራቸውንና ይህንኑም የሪፖርተር ጋዜጣ በመዘገቡ ጋዜጠኛውና ዋና አዘጋጁ ተከሰው በጎንደር ፖሊስ ተገደው መወሰዳቸው ይታወሳል፡፡ 
 
< Prev   Next >