Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ተነሱ
የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ተነሱ E-mail
Sunday, 05 October 2008
-ቤተሰቦቻቸው ሙሉ በሙሉ ከአገር ወጥተዋል

በአሰግድ ተፈራ

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ሀሰን በግምገማ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉ ተሰማ፡፡ ከሁለት ወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የክልሉን ባለሥልጣናትና የፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ ላይ አነጋግረው ነበር፡፡
የሪፖርተር ምንጮች እንዳስታወቁት ፕሬዚዳንቱ በግምገማ እንዲነሱ የደተረገው ፓርቲው ባካሄደው ስብሰባ ነው፡፡ በስብሰባው ወቅት በፕሬዚዳንቱ ከኃላፊነት መነሳት አስመልክቶ ተሰብሳቢዎች ለሁለት ተከፍለው ነበር፡፡

በ1999 ዓ.ም የግንቦት 20 ቀን የድል በዓል በጅጅጋ እየተከበረ ባለበት ሰዓት በድንገት በተወረወረ ቦምብ መጠነኛ ጉዳት ደርሶሳቸው የነበሩት ፕሬዳንት አብዱላሂ ልጆቻቸውን፣ ባለቤታቸውንና የባለቤቶቻቸውን ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ ከአገር እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ከፍተኛ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ነበር፡፡ አንዳንድ የክልሉ የፖለቲካ አመራሮች ጉዳዩን ቀደም ሲልም የታወቀ እንደሆነ ጠቁመው የፕሬዚዳንቱን ከኃላፊነት መነሳት ከሙስና ጋር ያያይዙታል፡፡ ሙስና ያሉትን ሲያብራሩም ገንዘብ በማስተላለፍ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡

ከሁለት ወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የክልሉን ባለሥልጣናት፣ የቢሮ ኃላፊዎችና የፓርቲውን (ሶህዴፓ) አመራሮች አዲስ አበባ በመሰብሰብ መውቀሳቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይናገራሉ፡፡ ሕዝቡ በአመራሩ ላይ ቅሬታ ስለሚያሰማ ማስተካከያ እንዲያደርጉ፣ በልማትና በፀጥታ ረገድ የሚወራውን ያህል እንዳልሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማስታወቃቸውን የዜናው ምንጮች አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሶህዴፓ ባደረገው ስብሰባ በስተመጨረሻ ፕሬዚዳንቱ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ቢወሰንም በስብሰባው ልዩነት እንደነበር ታውቋል፡፡ የዜናው ምንጮች እንዳሉት መከፋፈሉ ሙሉ በሙሉ መጥራት ይኖርበታል፡፡

በክልሉ ያለው ፀጥታ አስተማማኝ ከማድረግ አኳያ የጥንካሬ ችግር መኖሩን፣ ከልማት አንፃር ሕዝቡን በማሳተፍ ክልሉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት በዋናነት መታየት እንዳለበት የሚጠቁሙ አሉ፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የክልሉ ኃላፊ “ክልሉ ፕሬዚዳንት መቀያየር ልዩ መገለጫው ሆኗል፡፡” ብለዋል፡፡ በክልሉ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ሙስናና የልማት መስተጓጐል ይታያል፡፡ ፓርቲው በእነዚህ መሰረታዊ ችግሮች ላይ በማተኮር የሶማሌ ክልልን ገፅታ መቀየር ሲገባው ይህንን አላደረገም በማለት ቅሬታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ሶህዴፓ ከስምንት ወር በፊት የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር አምባሳደር መሐመድ ድሪርን ተራ አባል በማድረግ በሌላ መተካቱ የሚታወስ ነው፡፡

የተለያዩ ስብሰባዎች በክልሉ ለሚነሳ የሙስና ችግር ርምጃ ሲወስድ “ከፌዴራል የተመደቡትም ይጠየቃሉ” ቢባልም ተግባራዊ እንዳልሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መንግሥት ጉዳዩን እንዲያየው ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻ ያገኘነው ዜና እንደሚያመለክተው ከኃላፊነት የተነሱት ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ሀሰን ለጊዜው አዲስ አበባ ናቸው፡፡ እሳቸውን ተክቶ በፕሬዚዳንትነት የሚመራ ፕሬዚዳንት ለህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ይፋ በሆነ መንገድ አልተገለፀም፡፡
 
< Prev   Next >