Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚደርሱ...
በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚደርሱ... Print E-mail
Monday, 21 January 2008


በአፍሪካ ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ኤች.አይ.ቪን አስፋፍተዋል

በአፍሪካ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና የመብት ገፈፋዎች በሙሉ በአህጉሪቱ የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን ማስፋፋቱን የአፍሮል ኒውስ ዘገባ ያስረዳል፡፡ የፆታ ጥቃት ከሴቶች ተፈጥሯዊ የመጋለጥ ሁኔታ ጋር ተዳምሮ ሴቶቹ በአደጋ  እንዲሆኑ ማድረጉንም ዘገባው ጠቅሷል፡፡

የኢንተር አፍሪካ ኮሚቴ ተወካይ ለንዳ ኦስርሜን የአፍሪካውያን ማህበረሰቦች ባላቸው የአመለካከት ሁኔታና አወቃቀር ምክንያት ሴቶች መብታቸው በተገፈፈበት ሁኔታ ለዓመታት ዘልቀዋል፡፡

ዘገባው በተጨማሪም የአፍሪካ ሴቶች አህጉሪቱን እያጠቃ ባለው ጦርነት ምክንያትና በሰላማዊ ሁኔታዎችም ሳይቀር በተደጋጋሚ ለአስገድዶ መደፈር ለድብደባና ለመሳሰሉ ጥቃቶች ይጋለጣሉ፡፡

ለዚህ በምሳሌነት የተጠቀሰው ደግሞ በደቡብ ሱዳን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ሴቶች በየዕለቱ ለሚፈፀም ጥቃት መጋለጣቸውን ነው፤ ሴቶች በዚህ አካባቢ ይደፈራሉ፣ ይገደላሉ፣ ለባርነት ታፍነው ይወሰዳሉ፡፡

ሪሰርች አክሽን ኤንድ ኢንፎርሜሽን ኔትወርክ የተባለው በአፍሪካ ሴቶች ደህንነት ላይ የሚሠራ ተቋም በበኩሉ በአፍሪካ በሴቶች በልጃገረዶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ተገቢው  የተነፈገው መሆኑን ጠቅሰዋል ይላል ዘገባው፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ የተለያዩ ሀገሮች ገጠር የሚኖሩ ሴቶች ባሎቻቸው ከተሞች አካባቢ ቆይተው ሲመለሱ ኮንዶም ለመጠቀም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በኤች አይ ቪ እየተጠቁ ነው፡፡ በተለይ ለአስገድዶ መድፈር የሚዳረጉ ወጣት ሴቶች በተፈጥሮና የመራቢያ አካላታቸው ቫይረሱን ለመከላከል ያልዳበረ በመሆኑ ለኤች.አይ.ቪ የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍ ያለ ነው ይላል ዘገባው፡፡

 
< Prev   Next >