| የስፖርት ማዕከሉ በጥሩነሽ ዲባባ... |
|
| Sunday, 05 October 2008 | |
|
የስፖርት ማዕከሉ በጥሩነሽ ዲባባ ስም እንዲሰየም ተጠየቀ
በቤጂንግ ኦሊምፒክ ድል ላስመዘገቡና በውድድሩ ለተሳተፉ አትሌቶች ሐሙስ ዕለት በአሰላ ስተዲየም አቀባበል በተደረገበት ወቅት ተገኝተው የነበሩት ሚኒስትሯ፣ የኦሮሚያ ክልል ቀደም ሲል የእንሰሳትና የከብት ማርቢያ የነበረውን ማዕከል የብሔራዊ አትሌቶች ማፍሪያ ይሆን ዘንድ ለአትሌቲክስ ፌዴሬሽን መስጠቱንና አካዳሚውም በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ስም እንዲሰየም ጠይቋል፡፡ በአርሲ ለሚገነቧቸው የስፖርት ማዕከል መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ አስቴር፣ የማዕከሉ ግንባታ በዘንድሮው ዓመት ተጠናቅቆ በቀጣዩ ዓመት ስልጠና መስጠት እንደሚጀምር አመልክተዋል፡፡ በቀጣዮቹ ሶስት አመታትም በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሰልጥነው በለንደኑ ኦሊምፒክ የሚሳተፉ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ማፍራት እንደሚቻልም አክለው ገልፀዋል፡፡ ብቃት ያላቸው አሰልጣኞች፣ ዳኞችና ስፖርተኞች በአገሪቱ ባለመኖራቸው በስፖርቱ ዘርፍ የማስፈጸም ችግር የሚታይ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ ከኩባና ከቻይና ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት የተወሰኑ የውጭ አገር አሰልጣኞች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አዲስ በሚገነባው የስፖርት ማዕከልና በፌዴሬሽኖች ውስጥ የሚሰሩበት ሁኔታ መመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ |
|
| Last Updated ( Sunday, 05 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |