| የዲቪ ሎተሪ ለአመልካቾች ክፍት ሆነ |
|
| Sunday, 05 October 2008 | |
|
የአሜሪካ መንግሥት የ2010 ዲቪ ሎተሪ ከመስከረም 22 እስከ ህዳር 22 ቀን 2001 ባለው ጊዜ ማመልከት እንደሚቻል አስታወቀ፡፡
የአሜሪካ መንግሥት በየዓመቱ 50 ሺህ ያህል የሎተሪ ዕድለኞችን ወደ አገሩ እንዲገቡ በመፍቀድ የቋሚ ነዋሪነት ፈቃድ ይሰጣል፡፡ ኢትዮጵያም በየዓመቱ ከሶስት ሺህ በላይ ዕድለኞች የሎተሪው አሸናፊ ሆነው መቆየታቸው ታውቋል፡፡ ለ2010 ዲቪ አመልካቾች የትምህርት ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ወይም የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ ሶማሊያዊቷ ተሸለመች ሶማሊያዊቷ ሚስ አሻ ሐጂ ኦልተርኔቲቭ ኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሆኑ፡፡ የሶማሊያ ሴቶችና ሕፃናት ድርጅት መሥራች በመሆን የሕፃናትና የሴቶች ጥቃት እንዲቆም፣ ድህነትን ለመቀነስ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሚስ አሻ በተጨማሪም በተባበሩት መንግስታት ድጋፍ ባለፈው ግንቦት ወር በጅቡቲ በተካሄደው ስብሰባ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ሶማሊያ ያለ ቋሚ መንግሥት ላለፉት 17 ዓመታት መቆየቷን፣ በአሁኑ ወቅትም በእርስ በርስ ጦርነት ዜጎቿን እያጣች እንደምትገኝ ዘገባው ጠቅሷል፡፡ በኡጋንዳ ሰሜን ምዕራብ ግዛት የሕፃናት ሞት አሳሳቢ ሆኗል በሰሜናዊ ምዕራብ ኡጋንዳ ካርሞጃ ክልል ከጤና ጥበቃ ጉድለት ጋር በተያያዘ ሕፃናት ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ኢሪን ዘገበ፡፡ የኡጋንዳ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ችግሩን መከሰቱን በማመን ዘመቻ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ በአካባቢው ከዝቅተኛ የጤና አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ከ100 ሕፃናትና ታዳጊዎች መካከል አምስት ያህሉ በየሳምንቱ እንደሚሞቱ የጤና ጠቋሚ መረጃዎች አሳይተዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መረጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ካርሞጃ ግዛት ሕፃናት ከሚሞቱበት የዓለማችን አስቸጋሪ ስፍራዎች አንዱ ነው ብሎታል፡፡ ከካርሞጃ አካባቢ 1.1 ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚኖር አብዛኛው እርሻ ቀመስ አርብቶ አደሮች መሆናቸውን ዘገባው ያሳያል፡፡ በኡጋንዳ የጤና ሽፋን 72 በመቶ ሲሆን፣ በካርሞጆ አካባቢ ግን 24 በመቶ መሆኑን፣ ይህም የሚያሳየው በአካባቢው መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ጉድለት መኖሩን ነው ብሏል፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የሶማሊያን የባህር ዘራፊዎች ሊቀጣ ነው የአውሮፓ ኅብረት በሶማሊያ የባህር ዳር ዘራፊዎችን በጋራ ለመመከት የሚያስችል ኃይል መሰረተ፡፡ የፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስትር ቨርቪ ሞሪን ለቢቢሲ እንደገለፁት በሶማሊያ ያለውን የባሕር ላይ ዝርፊያ ለመመከት ቢያንስ ስምንት የአውሮፓ አገራት ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ የተፈፀመው አንድ 33 ታንኮችን የጫነች መርከብ ሶማሊያውያኑ በማገት 20 ሚሊዮን ዶላር መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡ በእንግሊዝ ሪፖርት መሠረት የሶማሊያ የባህር ላይ ዘራፊዎች በዚህ ዓመት ብቻ በ60 ያህል መርከቦች ላይ ጥቃት በማድረስ በተደጋጋሚ የገንዘብ ክፍያ ጠይቀዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በሶማሊያ ዋና ከተማ በሞቃዲሾ ሰሞኑን በሞርታር ጥቃት እንደደረሰባት፣ በጥቃቱም ሰባት ሰዎች መሞታቸውን ከ12 በላይ መቁሰላቸውን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ ባለፈው ረቡዕ በተጀመረው ጥቃት የአይን እማኞችን ጠቅሶ ቪኦኤ እንደዘገበው የሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ እንቅስቃሴ አልሻባብ በተሰኘው ቡድን ታግቷል፡፡ ቡድኑ አውሮፕላኖች መውጣትም ሆነ መግባት እንደማይችሉ አስጠንቅቋል፡፡ ለአልሻባብ ጥቃት የአፍሪካ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ እና የሽግግር መንግሥቱ ወታደሮች የአፀፋ ምላሽ እየሰጡ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |