| ሙስናን ለመከላከል 48 አዳዲስ... |
|
| Sunday, 05 October 2008 | |
|
ሙስናን ለመከላከል 48 አዳዲስ የአሰራር ጥናቶች ሊደረጉ ነው
አዳዲስ የአሠራር ስርዓት ጥናቶቹ ተግባራዊ ሲሆኑ ለሙስና ድርጊት ቀዳዳ የሚከፍቱ አሰራሮችን ለመከላከል እንደሚረዱ፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ለሙስና የተጋለጡ አሰራሮችን ለማስቀረትና ግንዛቤያቸውን ለማጎልበት እንደሚጠቅም አስታውቋል፡፡ (ዋኢማ) 110 የሺሻና ጫት ቤቶች ተዘጉ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሰዋ ዞን ፍቼ ከተማ 110 የሺሻና ጫት ቤቶች መዘጋታቸውን ፖሊሰ አስታወቀ፡፡ ቤቶቹ የተዘጉት በከተማዋ አራት ቀበሌዎች በተደረገ አሰሳ መሆኑን፣ ከ220 በላይ የሺሻ ማጨሻዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንና የሚጨስባቸውን የሚቃምባቸውን በመለየት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ እንዲሆኑ ከከተማው አስተዳደር ጋር ጥናት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) ለቅዱስ ያሬድ መታሰቢያ ሐውልት ለማቆም ዝግጅት ተጀመረ ለኢትዮጵያዊው የዜማና የውዝዋዜ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በአንድ ሚሊዮን ብር ወጭ የመታሰቢያ ሐውልት ለማቆም የሚያስችል ዝግጀት እየተፋጠነ መሆኑን የአክሱም ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ሕይወቱንም የሚተነትን ዶክመንተሪ ፊልም እንደሚዘጋጅም ገልጿል፡፡ ሐውልቱን ለማቆምና ዶክመንተሪ ፊልሙን በአፋጣኝ ለመስራት ከኅብረተሰቡ የተውጣጣ ሁለት ኮሚቴ መቋቋሙን፣ ሐውልቱ የሚቆመው ተወልዶ ባደገበት በአክሱም ከተማ አቅራቢያ ሙራደ ቃል በተባለ ስፍራ መሆኑን አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) ባለስልጣኑ ከኢታኖልና ከነዳጅ ጋር በተያያዘ ደረጃዎችን አፀደቀ የኢትዮጵያ የጥራትና ደረጃዎች ባለስልጣን ከኢታኖልና ከነዳጅ ጋር የተያያዙ አራት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ማጽደቁን አስታወቀ፡፡ ደረጃዎቹ የኢታኖል፣ የሞተር ዘይት፣ የኢታኖል ድብልቅ ነዳጅና የፔትሮሊየም ፈሳሽ የናሙና አወሳሰድን የሚመለከቱ መሆኑናቸውን ገልጿል፡፡ (ኢዜአ) ኖርዌይና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ተስማሙ በኢትዮጵያና ኖርዌይ መንግስታት መካከል ሻክሮ የነበረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኒዮርክ ከተማ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ተገናኝተው በሁለቱ አገሮች ዙሪያ መሞከራቸውን፣ ለሁለቱ አገሮች ግንኙነት መሻከር ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች ለማጣራት የተቋቋመው አጣሪ ቴክኒክ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ተወያይተዋል፡፡ (ዋኢማ) |
|
| Last Updated ( Monday, 06 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |