Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በናይጄሪያ የጎምቤ አስተዳደር ...
በናይጄሪያ የጎምቤ አስተዳደር ... E-mail
Sunday, 05 October 2008

በናይጄሪያ የጎምቤ አስተዳደር የገቢዎች ኮሚሽንን በስም ማጥፋት ወንጀል ከሰሰ

በናይጄሪያ የጎምቤ ግዛት አስተዳዳሪና ምክትል አስተዳዳሪ የሀገሪቱን የገቢዎች ኮሚሽንን በስም ማጥፋት ወንጀል መክሰሳቸውን ናይጄሪያን ትሪቡን ዘግቧል፡፡

 

አስተዳዳሪው ሙሐመድ ዳንጁማ ጎሬ እና ምክትል አስተዳዳሪው ጆን ላዛረስ ዮሪዮ ኮሚሽኑን በአቡጃ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የከሰሱት ኮሚሽኑ ባለፈው ሐምሌ ወር ሁለቱ ግለሰቦች በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ ሰብስበው ለግል ጥቅም ማዋላቸውን አስመልክቶ ለተለያዩ አካላት ደብዳቤ በመፃፉ ነው፡፡

የአስተዳዳሪዎቹ ጠበቃ ጋድዛማ ኮሚሽኑን ገንዘቡን እንዲመልሱ በመጠየቅ በፃፈው ደብዳቤና ለሰብሳቢው ሂማን ቱከር 750 ሚሊዮን የናይጄሪያ ብር መጠን ያለው የካሳ ክፍያ ጠይቀዋል፡፡

ሁለቱ አስተዳዳሪዎች ኮሚሽኑ ደብዳቤውን ለሌሎች አስተዳዳሪዎች፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤዎች፣ እንዲሁም ለሀገሪቱ እለታዊ ጋዜጦች በማሰራጨት መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካሄድ የቀደመ ሕይወታቸውን እንዲረበሽና በህብረተሰቡ ገንብተውት የነበረውን መልካም ስምና ስብዕና መናዱን ጠቅሰዋል፡፡

ክሱ የተሰበሰበውን ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ እንዳልተጠቀሙ ፍርድ ቤቱ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸውና ኮሚሽኑ በግዛቷ የገንዘብ አጠቃቀም ጉዳይ ብቃት የሌለው እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
 
< Prev   Next >