Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የዩጋንዳ መንግሥት በኮፒ ...
የዩጋንዳ መንግሥት በኮፒ ... E-mail
Sunday, 05 October 2008

የዩጋንዳ መንግሥት በኮፒ ራይት ጥሰት ተከሰሰ

የዩጋንዳ ብሄራዊ መዝሙር ያዘጋጁት ፕሮፌሰር ጆርጅ ዊልበር ፎርስ ካኮማ የዩጋንዳን መንግሥት በኮፒ ራይት ጥሰት በመክሰሳቸው መንግሥት የመከላከያ ጽሁፉን በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርብ መታዘዙን ዴይሊ ሞኒተር ዘግቧል፡፡

 

ፕሮፌሰር ካኮማ መንግሥትን በከፍተኛው ፍርድ ቤት የከሰሱት በብሄራዊ መዝሙር ስራቸው ላይ ያላቸው መብት ላይ ገደብ ተደርጎብኛል በሚል ሲሆን ለዚህም ካሳ እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል፡፡ ካኮማ ሀገሪቱ ለ45 ዓመታት የተገለገለችበትን ብሄራዊ መዝሙር ያዘጋጁት ከፒተር ዊንጋርድ ጋር በጋራ በመሆን ነበር፡፡

የከሳሹ ጠበቃ ጆታም ቱምዌሲግዮ ፕሮፌሰር ካኮማ እ.ኤ.አ በ1963 ከአዘጋጅ ኮሚቴው የተሰጣቸው 2"000 የዩጋንዳ ብር የምስጋና መግለጫ እንጂ ከፍያቸው እንዳልሆነ ተከራክረዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ1964 የወጣው የሀገሪቱ የኮፒ ራይት ሕግ ክፍል 4 እና 9 እ.ኤ.አ በ2006 በወጣው የኮፒ ራይትና ተዛማጅ መብቶች ሕግ ውስጥ እንዳለ የተያዘ ሲሆን ክፍሎቹ አንድ ክፍያ የተፈጸመለት ግለሰብ የአእምሯዊ መብት ጥያቄን ማንሳት እንዳይችል ይከለክላሉ፡፡

ፕሮፌሰሩ ባለፉት አርባ አምስት ዓመታት ክፍያው እንዲፈፀምላቸው ሲጠይቁ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ዴይሊ ሞኒተር ፕሮፌሰር ካኮማ የፒርስ አፍሪካ የሕይወት ዘመን ስኬትን ጨምሮ የበርካታ ሽልማቶች ባለቤት መሆናቸውን ዘግቧል፡፡  
 
< Prev   Next >