| በአሸባሪነት የተጠረጠሩ የኬንያ... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
![]() ሰይድ ሀማሲ መሀመድ ከቤተሰቦቹ ጋር ሲቀላቀል በጋዜጣው ሪፖርተር በአሸባሪነት ተጠርጥረው ላለፈው አንድ ዓመት በኢትዮጵያ በእስር የቆዩ ስምንት የኬንያ ዜጎች ነፃ ተለቀው ኬንያ መግባታቸውን የቢቢሲ ዘገባ አመለከተ፡፡ ግለሰቦቹ በእስር የቆዩት በኢትዮጵያ ወታደሮች የተበታተነው የሶማሊያ እስላማዊ ፍ/ቤቶች ህብረት አባላት ናቸው ተብለው ተጠርጥረው በ1999 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ከዋሉ ጀምሮ ነው፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ተማጓቾችና የሙስሊም ህብረተሰብ ቡድኖች ግለሰቦቹ ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡት፣ የኬንያ መንግሥት በሶማሊያ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኬንያ የተሰደዱ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎች ላይ ባደረገው አሰሳ ነው፡፡ አንድ የኬንያ ባለስልጣን እንዳሳወቁት፣ ስምንቱ ተጠርጣሪዎች በነፃ ተለቀው ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ "ከሶማሊያ ዓማፂ ቡድኖች ሆነው ሲዋጉ የነበሩት ስምንት የኬንያ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ በቁጥጥር ስር የነበሩ ቢሆንም፣ በነፃ ተለቀው ወደ ኬንያ አገራቸው ተመልሰዋል" ሲል የኬንያ መንግሥት ቃል አቀባይ አልፍሆድ ሙታ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል፡፡ ባለስልጣኑ ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ "ኬንያውያኑ እ.ኤ.አ በ2006 ወደ ሶማልያ የሄዱት ወታደራዊ ስልጠና ለማግኘት እንደሆነና ቀጥለውም በደቡብ ሶማሊያ ውስጥ በሚገኙት አሸባሪዎች መመልመላቸውን ምርመራው ያመላክታል" ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል አንድ የኬንያ ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ጠበቃ፣ የኬንያ መንግሥት በመጀመሪያ ለምን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ እንደሰጣቸው ተጠርጣሪዎቹ ክስ እንዲመሰርቱ እንደሚተባበራቸው መናገሩን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ተቀማጭነቱን አሜሪካ ያደረገው ሂዶማን ራይትስ ዎች በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት የእስረኞች አያያዝ እንደሚያሳስበው አሳውቋል፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት ቡድኑ ባወጣው መግለጫ፣ ከ150 በላይ የተለያየ ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች ከእስላማዊ ፍ/ቤቶች ህብረት ጋር ጦርነት በነበረ ወቅት በሶማሊያ ባህር ጠረፍ አካባቢ የተያዙ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ ቢቢሲ ባደረገው ምርምር በአዲስ አበባ የሚገኙት እስረኞች አያያዝ ደካማ መሆኑንና ከተማዋ "የአፍሪካ ጓንታናሞ" መሆኗን ገል"ል፡፡ በከተማዋ የነበሩት እነዚህ እስረኞች በአፍሪካ የመጀመሪያው ሰለቫዎችና ጅምላዊ የአሸባሪነት ተጠርጣሪዎች በማለት ገል"ቸዋል፡፡ የኬንያው ቃል አቀባይ ሚስተር ሙታ፣ ተጠርጣሪዎቹን ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው የተሰጡበትን ሁኔታ ሲያስረዱ፣ የሶማሊያ ዜጎች ነን በማለታቸው ወደ ሶማሊያ መወሰዳቸውና ከዚያ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን ገልፀዋል፡፡ |
|
| Last Updated ( Thursday, 09 October 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |