Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow በሶማሌ ክልል ሹም ሽር ቀጥሏል
በሶማሌ ክልል ሹም ሽር ቀጥሏል E-mail
Wednesday, 08 October 2008
- የፖሊስ መኮንኖችና የቢሮ ኃላፊዎች ተነሱ

በአሰግድ ተፈራ

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመሩት ውይይት መነሻነት በሶማሌ ክልል እየተከናወነ ያለው የመዋቅር ማጥራት ሥራ ጋር በተያያዘ ሹም ሽር እየተካሄደ መሆኑን አንድ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን አስታወቁ፡፡

የክልሉን ባለስልጣናት የፓርቲ አመራሮች አዲስ አበባ አስጠርተው በሶማሌ ህዝብ ላይ መዥገር ሆናችሁበታል በማለት በክልሉ ለውጥ ማምጣት ያልቻሉትን ባለስልጣናት መውቀሳቸውን በስብሰባው ላይ የተገኙ ተናግረዋል፡፡

የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) መዋቅሩን እንዲያስተካክል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጽንኦት እንዳሳሰቡ፣ ይህንንም ተከትሎ ፓርቲው በቀጥታ ወደ ግምገማ መግባቱንና ፕሬዚዳንቱን ከኃላፊነት እንዳነሳ የገለፁት ባለስልጣኑ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ ኃይሎችና የተለያዩ የመዋቅር አባላት ላይ ርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የመዋቅር ማጥራት ሥራው ከመልሶ ማደራጀት ጋር ጎን ለጎን እየተካሄደ መሆኑን የገለፁት ባለስልጣኑ በሶማሌ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ንክኪ ያላቸው የፀጥታ ኃይሎች እንዲባረሩ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከላካቸው ባለሙያዎች ጋር በመሆን የክልሉን የፋይናንስ ስርዓት ሙሉ በሙሉ የመቀየሩ ሥራ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ የገለፁት ባለስልጣኑ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 50 የሚሆኑ የተለያዩ የአመራር አካላት ከኃላፊናቸው መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከጥቂት በስተቀር ሙሉ በሙሉ የቢሮ ኃላፊዎችና ምክትሎቻቸው፣ የፕሬዚዳንት ቢሮ አካባቢ ይሰሩ የነበሩ ሠራተኞችም እንዲወገዱ ተደርጓል፡፡

በሶማሌ ክልል ፀጥታ ጋር በተያያዘ ችግር ያለባቸው አመራሮች ላይ ርምጃ አልወስዱም፣ ጠንካራ አመራሮች ወደ ኃላፊነት እንዲመጡ አላደረጉም፣ ከጥገኛ ባለሃብቶችና ኮንትራክተሮች ጋር ትስስር በመፍጠር በግል በልጽገዋል በሚል ተገምግመው ከፕሬዚዳንትነታቸው፣ ከፓርቲው ሥራ አስፈፃሚና ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲነሱ "የፖለቲካ ውሳኔ" የተወሰነባቸው ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ሀሰን በተደጋጋሚ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ ቢመከሩም ምክሩን ተግባራዊ ሊያደርጉ እንዳልቻሉ ፓርቲያቸው ያወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በተገመገሙበት ጉዳይ ተጨባጭ ማስረጃ እየተሰበሰበ ቢሆንም ክስ ይመሰረትባቸው አይመስረትባቸው ያልጠቆሙት ባለስልጣኑ የክልሉ ፓርላማ አባል መሆናቸውን ገልፀው ያለመከሰስ መብት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ አዲስ አበባ እንዲመጡ መደረጉንና የሳቸውና የባለቤቶቻቸው ቤተሰቦች ሙሉ በሙሉ ከአገር ማስወጣታቸውን ገልፀን ባለፈው ሳምንት እሁድ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በቅርቡ የፌዴራሉ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፌዴራል አገር ውስጥ ጉዳይ፣ ለፓርላማና ለህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ በፃፈው ደብዳቤ በኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጉዳት የደረሰባቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ጎሳዎች ችግራቸውን አስመልክቶ ለክልሉ መንግስት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም "ጉዳዩ ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ነው" የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

250ሺ የሚጠጉ የፊቅ ኦማር ሼካሽ ጎሳ አባላት ከመኖሪያ ቀያቸው ተሰደው በሶማሌና በኦሮሚያ ባሌ ዞን አዋሳኝ ራሶ በምትባል ቀበሌ መስፈራቸውን የኮሚሽኑ ደብዳቤ ያስረዳል፡፡
 
< Prev   Next >