| የመንግሥት የአደረጃጀት ለውጥ... |
|
| Wednesday, 08 October 2008 | |
|
የመንግሥት የአደረጃጀት ለውጥ ውሣኔ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሕግ ሊሰጥ ነው
በፍሬው አበበ መንግሥት የአደረጃጀት ለውጦች በሚያስፈልጉት ጊዜ፣ ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ማስፀደቅ ሳያስፈልግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ብቻ ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ነገ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው፡፡ ምንጮች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት አዲሱ ረቂቅ አዋጅ በመንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ኤጀንሲዎች፣ ኮሚሽኖች እና የመሳሰሉት መንግስታዊ ተቋማት የአደረጃጀት ለውጥ ማድረግ ሲያስፈልግ ለፓርላማ አቅርቦ ማስፀደቅ ያስፈልግ የነበረውን አሠራር የሚሽር ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ሰኞ ከቀትር በኋላ የፓርላማውን 4ኛ የሥራ ዘመን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ለውጡን ማድረግ ያስፈለገው የመንግሥትን አመራርና አገልግሎትን ለማሻሻል በተለይም ደግሞ ከሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም ተግባራዊነት ጋር በማዛመድ የተለያዩ የመንግሥት አደረጃጀት ለውጥ ማድረግ በማስፈለጉ መሆኑን መጠቆማቸው ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በነገው ዕለት የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ወደ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው እንደሚቀርብ ምንጫችን ጠቁሟል፡፡ በፕሬዚዳንት ግርማ ንግግር መሠረት ዘንድሮ የአደረጃጀት ለውጥ ከሚደረግባችው መሥሪያ ቤቶች መካከል የማስታወቂያ ሚኒስቴር ይገኝበታል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |