Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እድሜያቸው...
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እድሜያቸው... E-mail
Wednesday, 08 October 2008
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እድሜያቸው ከ35 አመት በላይ የሆኑ የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ተቀበለ

በኃይሌ ሙሉ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እድሜያቸው ከ35 አመት በላይ የሆኑ ለድህረ ምረቃ ያለፉ ተማሪዎችን አልቀበልም ብሎ ያሳለፈውን ውሳኔ አስተካክሎ ተማሪዎቹን ለመቀበል ወሰነ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምንጮቻችን እንደገለፁልን የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የፋኩልቲ ዲኖች ተሰብስበው ባስተላለፉት ውሳኔ መሰረት ዩኒቨርሲቲው እድሜያቸው ከ35 አመት በላይ የሆኑ ተፈታኞች በድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ወስኖ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ ከፕሬዚዳንት ቢሮ በመጣ መመሪያ መሰረት ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈተናዎች ያለፉ ተማሪዎች ተቀባይነት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

ምንጮቻችን እንደሚሉት ዩኒቨርሲቲው ከ35 አመት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን አልቀበልም ብሎ ያስተላለፈው ውሳኔ በኢዱኬሽን ፋኩልቲ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡ ኢዱኬሽን ፋኩልቲ መመሪያውን በመቃወም ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን መቀበሉና ሌሎች ፋኩልቲዎች ደግሞ ከ35 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን አንቀበልም ማለታቸው በአተገባበር ላይ ልዩነት ፈጥሮ ነበር፡፡

እድሜያችሁ ከ35 ዓመት በላይ ነው ተብለው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ተከልክለው የነበሩ ተማሪዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሚመዘግብበት ጊዜ እድሜ ፈተናውን የማለፊያ መስፈርት መሆኑን አልገለጸም ነበር፡፡ ስራቸውን ለቅቀውና ቤት ተከራይተው መኖር ጀምረው የነበሩ ሰዎችም በዩኒቨርሲቲው ውሳኔ ተደናግጠው እንደነበር እነዚሁ ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡

የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን የዕድሜ ጣሪያ ከ35 አመት በታች መሆን አለበት የሚለውን መመሪያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መቼ እንደሚተገብረው ምንጮቻችን ያሉት የለም፡፡
 
< Prev   Next >